Page 43 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 43
34
ጥ
ታ ቁ
ሽ
ጥር
በ
በሽታ ቁጥጥር
የተለያዩ የአመራረት ዘዴዎችንና የበሽታ መከላከያ ዘዴዎችን አሰባጥሮበመጠቀም ዳውን
ሚሊዲውን ለመቆጣጠር ይቻላል፡፡ ከነዚህም ዘዴዎች ውስጥ፡
• በሽታውን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን መጠቀም፤
• የዘር ጥራትን መጠበቅ ማለትም በሚገባ የታከመ ዘር መጠቀም፤
• አፈር ላይ የተብላላ ብስባሽ ወይም ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ መጠቀምና ማሳን በሚገባ
ማዘጋጀት ተክሎች ግዙፍና ጤናማ እንዲሆኑ ማድረግ፤
• ከሁለት የቅጠል ደረጃ ጀምሮ እስከ አበባ ወይም የፍሬ ጭንቅላት ማውጣት ያለው የእድገት
ደረጃ የኬነዋ ተክል ለዚህ በሽታ በጣም የሚጋለጥበት ወቅት ስለሆነ፤ የተከላ ጊዜን
በማስተካከል ከፍተኛ ዝናብ የሚኖርበት ወቅት ከዚህ የእድገት ደረጃ ጋር እንዳይገጣጠም
ማድረግ፤
• ለአካባቢው ሁኔታ ተስማሚ የሆነ የተክል ቁጥር መጠቀም፡፡ ለምሳሌ ከፍተኛ የአየር
እርጥበት ባለበት ቦታ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በመስመሮች መካከል ከ 0.5 ሜትርና
በተክሎች መካከል ከ0.15 ሜትር ያላነሰ እርቀት እንዲኖር ማድረግ፤
• በማሳ ውስጥ የሚፈጠር ትርፍ ውሃን በወቅቱ እንዲንጣፈፍ ማድረግና፤
• አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ተገቢውንአይነት ጸረ-ፈንገስኬሚካል መጠቀም፤ ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡
ና ድ
ህ
ብሰ
ብ
ዝ
ረ ም
ር
ት አ
ያ
ያ
ም
7. 7. የምርት አሰብሰብና ድህረ ምርት አያያዝ
የ
ሰ
ት አ
ር
እንደ ዝርያው አይነትና እንደ አካባቢው ልዩ ሁኔታ በአንዲስ አካባቢ የሚገኘው የኬነዋ ምርት
በሄክታር ከ 400 እስከ 1200 ኪ.ግ ይደርሳል፡፡ ነገር ግን የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት
የኬነዋ የምርት አቅም በሄክታር እስከ 11 ቶን ይደርሳል፡፡ በሃገራችን የማስተዋወቅ ስራዎች
በተሰሩባቸው የአማራና የኦሮሚያ ክልል በሄክታር በአማካኝ እስከ 20 ኩንታል የተገኘ ሲሆን
ከፍተኛ ተብሎ የተመዘገበው 45 ኩንታል ነው፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል