Page 48 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 48
39
ምስል 43. በመጨረሻ የተጣራው እህል ዉሃ በማያስገባ እቃ መቀመጥ አለበት
8 . ኬ ነ ዋ ን በ መ ስ ኖ የ ማ ም ረ ት ዘ ዴ
8. ኬነዋን በመስኖ የማምረት ዘዴ
ኬነዋ የመስኖ ዉሃ ባለበት አካባቢ ከሌሎች ሰብሎች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ በሆነ የዉሃ ፍጆታ
ሊመረት ይችላል፡፡ ኬነዋን በመስኖ ለማምረት፤ በመጀመሪያ የሚመረትበትን ቦታ አርሶ በሚገባ
ማለስለስ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ በመቀጠል የዉሃ ማጠጫ ቦዮች በየአርባ ሳንቲ ሜትር ርቀት
ይሰራሉ፡፡ የዉሃ ማጠጫ ቦዮቹ ርዝመት እንደ መሬቱ ወጣ-ገባነት ይወሰናል፡፡ መሬቱ እምብዛም
ወጣ-ገባ ባልሆነበት ቦታ የቦዮችን ርዝመት እስከ አስር ሜትር ድረስ ማስረዘም ይቻላል፡፡ ነገር
ግን መሬቱ በጣም ወጣ-ገባ ከሆነ ቦዮች እስከ አምስት ሜትር ድረስ ሊያጥሩ ይችላል፡፡
ቦይ ከተዘጋጀ በኋላ ትክክለኛ የመዝሪያ መስመሮችን ለመወሰንና ቦዮችን ለማስተካከል እንዲረዳ
ዘር ከማፍሰሳችን በፊት ማሳውን ዉሃ ማጠጣት ያስፈልጋል፡፡ ዉሃ በሚጠጣበት ወቅት ዉሃው
በጣም የሚንደረደር ከሆነ፤ ዉሃ መግቢያ አካባቢ ያሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች ዝቅ እንዲሉ መደረግ
አለበት፡፡ ዉሃው ወደ ኋላ ለመመለስ የሚሞክር ከሆነ ደግሞ በቦዩ እርዝመት መሃል ላይ ወይም
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል