Page 50 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 50
41
ወቅት ተክሎች እንዳይወድቁ ያደርጋል፡፡ አጠቃላይ የኬነዋው ማሳ ቢጫ መሆን ከጀመረ በኋላ
ዉሃ መስጠት ማቋረጥ ያስፈልጋል፡፡
9 . ዘ ር በ ማ ም ረ ት ወ ቅ ት የ ሚ ደ ረ ጉ ጥ ን ቃ ቄ ዎ ች
9. ዘር በማምረት ወቅት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች
ምንም እንኳን ኬነዋ ራስ በራስ የብናኝ ዘር ልውውጥ የሚራባ ቢሆንም እስከ 15 ከመቶ
የሚደርስ ተሻጋሪ የብናኝ ዘር ልውውጥ ያካሂዳል፡፡ ስለዚህ የተለያዩ ዝርያዎች ተጠጋግተው
ከተዘሩ እርስ በእርስ ሊዳቀሉና መሰረታዊ ባህሪያቸውን ሊያጡ ይችላሉ፡፡ ኬነዋ በጣም ትንንሽና
ቀላል ክብደት ያለቸው ብናኝ ዘር ስለሚያመርት ብናኝ ዘሮቹ በንፋስ አማካይነት እረጅም
ርቀት ይጓዛሉ፡፡ በመሆኑም በዝርያዎች መካከል ያልተፈለገ መዳቀል እንዳይኖር በዝርያዎች
መካከል ከሶስት እስከ ስምንት ኪ.ሜ ርቀት መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም እንደ ዳውኒ
ሚልዲው ያሉ በሽታዎች በዘር ላይ በመጣበቅ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላው ከአንድ የምርት ዘመን
ወደ ቀጣዩ ይተላለፋሉ፡፡ በመሆኑም በዚህ በሽታ መጠቃቱ ከታወቀ ማሳ ላይ የሚገኝዘርን
ለተከላ አለመጠቀም ወይም ከመጠቀማችን በፊት ዘሩን በማከም የበሽታውን አምጪ ተዋህስ
ማስወገድ ያስፈልጋል፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል