Page 52 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 52

43

         ማሽላ  ውስጥ  ከሚገኘው  በአራት  እጥፍ  የበለጠ  ሲሆን  በጤፍ፣  በስንዴና  በገብስ  ውስጥ

         ከሚገኘው ደግሞ በእጥፍ ይበልጣል (ሰንጠረዥ 3) ፡፡ እንዲሁም የአሚኖአሲድ አይነቶች
         ላያሲን፣ ሜቲዮኒን፣ ትሪዮኒንና ትሪፕቶፋን ሲሆኑ እነዚህም ኬነዋ ውስጥ በበቂ ሁኔታ ይገኛሉ፡፡




               ግ
                 ብ ቅ
         1
              ም
                     ባ
                      ት
           2 የ
               11.2 የምግብ ቅባት
          1
          .
         በሰንጠረዥ አንድ ላይ እንደተመለከተው በ100 ግራም ፍሬ ውስጥ በ አማካኝ 6 ግራም ቅባት
         የሚይዝ ሲሆን ይህም በሃገራችን የተለመዱት እህሎች ከሚይዙት እጅግ የበለጠ ነው፡፡ ቅባት
         ለሰውነታችን ጉልበት ከሚሰጡ ንጥረ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከመሆኑም በላይ በቅባት የሚሟሙ
         የቫይታሚን አይነቶችን ወደ ሰውነትውስጥ ለማስረጽ ይረዳል፡፡ ኬነዋ ውስጥ ከሚገኘው ጠቅላላ
         ቅባት ውስጥ ከመቶ ወደ ዘጠና እጅ የሚሆነው አንሳቹሬትድ (ጤነኛ አይነት) ሲሆን ከዚህም

         ውስጥ ግማሽ የሚሆነው አስፈላጊ የሆኑ ኦሜጋ 6 እና ኦሜጋ 3 የሚባሉት የቅባት አይነቶች

         ናቸው፡፡  እነዚህ  የቅባት  አይነቶችን  ሰውነታችን  በራሱ  ሊያዘጋጃቸውስለማይችል  የግድ
         በምንመገበው ምግብ ውስጥ መገኘት አለባቸው፡፡ ኬነዋ በውስጡ ቫይታሚን ኢ የሚባለውን

         ንጥረ ነገር በመያዙ ምክንያት ከኬነዋ የሚገኝ ዘይት ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ መቆየት ይችላል፡፡


              ር
                       ት
                        / ሃ
                    ድ
                  ይ
                     ሬ
               ቦ ሃ
           3 ካ
                          ይ
                               ጪ
               11.3 ካርቦ ሃይድሬት/ ሃይል ሰጪ
                            ል ሰ
          .
          1
         1
         በ100 ግራም የእህል ዘር ውስጥከ 60 እስከ 70ግ የሚሆነው ስታርች ነው፡፡ ስታርች ደግሞ ካርቦ
         ሃይድሬትን በማመንጨት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ በኬነዋ ውስጥ ከ 58 እስከ 68 በመቶ
         የሚሆነው እስታርች ሲሆን 5 ከመቶ የሚሆነው ደግሞ ስኳር ነው፡፡ በተጨማሪም  ካለው
         ቀስ በቀስ የሚዋሃድ ስታርች ተዳምሮ ኬነዋን በዝግታ ወደ ሰውነት የሚሰርጽ የሃይል ምንጭ
         ስለሚያደርገው ለጤንነት ተስማሚ ነው፡፡ ይህ የያዘው ከፍተኛጥራት ያለው ስታርችና ዝቅተኛ
         መጠን ያለው ግሉኮስና ፍሩክቶስ ኬነዋን ዝቅተኛ ግላይሴሚክ ኢንዴክስ ካርቦ ሃይድሬት ያለው
         ያደርገዋል፡፡ ይህም ማለት ከኬነዋ የሚገኝ ካርቦ ሃይድሬት የደምን የስኳር መጠን አይጨምርም




 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል  የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   47   48   49   50   51   52   53   54   55   56   57