Page 57 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 57

48
        ሳፖኒንበተለያዩ ቦታዎች የተቀናጀ የተባይ መከላከያ ግብአት ሆኖ ያገለግላል፡፡ በሃገራችን ደሃና

        በሚባለው ወረዳ አካባቢ ከተገኘ የአርሶ አደሮች ተሞክሮ ለመረዳት እንደሚቻለው፤ በምግብ

        ዝግጅት ወቅት በፍተጋም ሆነ በማጠብ ከኬነዋ ዘር ላይ የተወገደ ሳፖኒን የከብቶችን የውጭ

        ጥገኛ ተባዮችን ለማጥፋት ይረዳል፡፡




        እስካሁን  ባለው  ሁኔታ  በግለሰብ  ደረጃ  ሊተገበሩ  የሚችሉ  ሳፖኒን  ማስወገጃ  ዘዴዎች  ዘሩን

        በውሃ ማጠብ፣ መፈተግና ሁለቱን ዘዴዎች (ማለትም ማጠብና መፈተግን) ማቀናጀት ናቸው::
        በሃገራችን  በገጠራማ  አካባቢዎች  ካለው  የዉሃ  እጥረት  አኳያ  ሳፖኒን  በዉሃ  አጥቦ  ሙሉ

        በሙሉ ማስወገድ ከፍተኛ የሆነ የዉሃ ፍጆታ ያስከትላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፍተጋ ብቻውን

        ሊያስወግደው የሚችለው የሳፖኒን መጠን እስከ 95 ከመቶ የሚሆነውን ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም

        ሁለቱን ዘዴዎች በማቀናጀት በአነስተኛ የዉሃ ፍጆታ (ቀሪውን 5 ከመቶ ሳፖኒን ለማስወገድ)

        የተሻለ ውጤት ለማግኘት ይቻላል፡፡ ኬነዋን በእጥበት ለማስወገድ ከቀዝቃዛ ዉሃ ይልቅ የሞቀ

        ወይም አሲዳማ (ዉሃ አጋር የተደረገበት) ወይም ኮምጣጣ (ቤኪንግ ሶዳ የተቀላቀለበት) ዉሃ

        የተሻለ ውጤት ይሰጣል፡፡ ነገር ግን እነዚህን ኬሚካሎች በምን ያህል ብንጠቀም ጥሩ ውጤት
        እናገኛለን የሚለው ጥናት ይፈልጋል፡፡ በአጠባ ሳፖኒንን በሚጸዳበት ወቅት ዉሃው እየተቀየረ

        ዘሩ ሲታጠብ አረፋ መስራት ሲያቆም ሳፖኒኑ ታጥቦ ማለቁን ያሳየናል፡፡ምንም እንኳን በሃገራችን

        ባይሞከርም በአንዳንድ አገሮች ሳፖኒንን ለማስወገድ ዘሩን በመጠኑ በእሳት ካመሱ በኋላ (ወደ

        ቡናማ ሲቀየር) ሙቀቱ ሳይለቅ ፈትጎ ማንፈስና ማጠብ (ምስል 45)፡፡

















                                        የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል     የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   52   53   54   55   56   57   58   59   60   61   62