Page 53 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 53
44
ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ኬነዋ የማይፈተግ የእህል አይነት ስለሆነ (የሚወገድ የዘር ሽፋን
ስለሌለው) ተፈትገው ወይም በፋብሪካ ተቀነባብረው ለምግብነት ከሚውሉት ሌሎች የእህል
አይነቶች ጋር ሲነጻጸር ሰውነታችን ሊፈጨው የሚችለው በዝግታ ስለሆነ ለረጅም ጊዜ የረሃብ
ስሜት እንዳይሰማን ከማድረጉም በላይ የደም የስኳር መጠን ሳይዋዥቅ እንዲቆይ ስለሚያደርግ
የሰውነት የጉልበት (ኢነርጂ) ፍላጎትም እንዳይዋዥቅ ያደርጋል፡፡
.
4
1 11.4 አሰር
1
ሰ
ር
አ
ኬነዋ ከፍተኛ መጠን ያለው አሰር የያዘ ሲሆን የፍሬው ጠቅላላ ክብደት እስከ 6 ከመቶ
ይደርሳል:: ይህ ከፍተኛ የፋይበር ይዘት ምግብ በአንጀት ውስጥ የሚያደርገውን ዝውውር
በማፋጠን፣ የኮሊስትሮል መጠንን በመቆጣጠርና አስፈላጊ የሆኑ ባክቴሪያዎች እንዲፈጠሩ
በማድረግ የጨጓራ ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል፡፡በአጠቃላይ ከእህል የሚሰሩ በተለይ ደግሞ
ከኬነዋ የሚዘጋጁ ምግቦች ውሃ የመያዝና ለረጅም ጊዜ ሳይፈጩ የመቆየት ባህሪ ስላላቸው
የጥጋብ ስሜትን ስለሚፈጥሩ ቶሎ ቶሎ በመመገብ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
ኬነዋ ዝቅተኛ የግሉተን መጠን ከመያዙም በተጨማሪ በግሉተን ከፍተኛ ይዘታቸው ከሚታወቁት
ሰብሎች ጋር ምንም አይነት ቤተሰባዊ ዝምድና የሌለው በመሆኑ በግሉተን ኢንቶለራንስ
(አለርጂ) ለሚጠቁ በሽተኞች አዲስ አማራጭ ሰብል ነው፡፡
ና
ድ
ይ
ት
ና ቫ
ች
11.5 ማእድናትና ቫይታሚኖች
ኖ
ታ
ሚ
.
5 ማ
1
1
እ
በአማካይ ኬነዋ ከጤፍና ከቦለቄ በቀር ከሌሎች ሰብሎች የተሻለ የሚኒራል ይዘት አለው
(ሰንጠረዥ 4). ኬነዋ የአማካይ ሰውን የቀን ፍላጎት መሰረት ባደረገ ስሌት በተለይ የብረት፣
የማግኒዚየምና የዚንክ ጥሩ ምንጭ ነው፡፡
ሠንጠረዥ1፡ የኬነዋ የዋና ዋና ንጥረነገሮች ይዘት (በ100 ግራም ውስጥ) ከሌሎች በኢትዮጵያ
ከተለመዱ ሰብሎች ጋር ሲነጻጸር
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል