Page 49 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 49
40
መጨረሻ አካባቢ ያሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች ዝቅ እንዲሉ መደረግ አለበት፡፡ ማሳው ከጠጣ በማግስቱ
በሚገባ ጠፈፍ ካለ በኋላ በየቦዩ ውስጥ ዉሃው ደርሶ የነበረበትን ከፍታ ተከትሎ መስመር
በመስራት ዘሮችን ማንጠባጠብና በእርጥብ ነገር ግን በሚፈረፈር አፈር ማልበስ፡፡ ከዚህ በኋላ
ኬነዋው በቅሎ ሙሉ በሙሉ ከአፈር ውስጥ እስኪወጣ ድረስ ማሳው ዉሃ አይሰጠውም፡፡
ከዚያ በኋላ ችግኞች አንድ ጥንድ እውነተኛ ቅጠል እስከሚያወጡ ድረስ፤ በዉሃ እንዳይታጠቡ
በየሶስት ቀኑ ቀለል ያለ (ቦዮችን ለማርጠብ ያህል ብቻ) መስኖ እንዲሰጣቸው ይደረጋል::
የመጀመሪያውን ጥንድ ቅጠል ካወጡ በኋላ፤ ቅጠሎች ጠዋት ወይም ወደ ማታ ላይ
የሚያሳዩትን የመጠውለግ ምልክት እያስተዋሉ ዉሃ መስጠት::: ችግኞች ሁለት ጥንድ እውነተኛ
ቅጠል ሲያወጡ (ምስል 44)፤ በአንድ ቦታ ሁለት ሁለት ችግኞችን በመተው በየአስር ሳንቲ
ሜትር እርቀት ማሳሳት:: ከዚያም ችግኞች አራት ጥንድ ቅጠል ሲያወጡ፤ ከሁለቱ የተሻለውን
በማስቀረት ሌላኛውን መንቀል ያስፈልጋል፡፡ በማሳሳትም ሆነ በነቀላ ወቅት ቀሪዎቹ ችግኞች
እንዳይነቀሉ ወይም ስራቸው እንዳይናጋ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ዘር
በምናፈስበት ወቅት ተጠጋግተው የሚወድቁ ዘሮች የሚያበቅሉት ስር እርስ በርሱ የተጠላለፈ
ሊሆን ስለሚችል ነው፡፡
በመስኖ የሚመረት ኬነዋ የሚፈልገው የማዳበሪያ
መጠንም ሆነ የማድረጊያው ወቅት በዝናብ ከሚመረት
ኬነዋ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ማዳበሪያ ከተደረገ በኋላ
ማዳበሪያ በዉሃ እንዳይጠረግ ከማዳበሪያ በኋላ
የሚደረግ መስኖ ቀለል ያለ መሆን አለበት፡፡ ማሳው
በሚሳሳበት ወቅት፣ ማዳበሪያ በሚደረግበት ወቅትና
በአረም ወቅት ኬነዋውን አፈር ማስታቀፍ፤ በምርት
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል