Page 44 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 44
35
.
1
.
7.1. ም ር ት የ መ ድ ረ ሱ ም ል ክቶ ች
7
ምርት የመድረሱ ምልክቶች
የኬነዋ ተክል እድሜ በጨመረ ቁጥር የዘሩ ራስ አይነተኛ ወደ ሆነውና የምርት መድረስን ወደ
ሚያበስረው ቢጫ ቀለም ከመቀየሩ በፊት ቅጠሉ ጠቆር ያለ አረንጓዴ ይሆናል (ምስል 38-2)::
ለምርት በሚደርስበት ወቅት ተክሉ ከላይ ወደታች ቢጫ እየሆነ ይሄዳል ፡፡ ስለሆነም ፍሬው
ለመሰብሰብ ደርሶ ሳለ ቅጠሎቹ አረንጓዴ ሆነው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ የዘሩ ራስና ቅጠሎቹ ጠቆር
ያለ አረንጓዴ ከሆኑ ጀምሮ እስከ 15 ቀናት በሚሆን ጊዜ የአንዳንድ ተክሎች የዘር ጭንቅላት
ወደ ቢጫነት መቀየር ይጀምራል (ምስል 38-3)፡፡ የአንዳንድ ተክሎች የዘር እራስ ቢጫ መሆን
ከጀመረ በኋላ እስከ ስምንት ቀናት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተክሎች የዘር ጭንቅላት
ቢጫ ይሆናል (ምስል 38-4 ):: ከዚያም የያንዳንዱ ተክል የዘር እራስ ሙሉ በሙሉ ቢጫ ከሆነ
በኋላ በዘሩ እራስ ውስጥ ያሉት ቅጠሎች ወደ ቢጫነት መቀየር ይጀምራሉ (ምስል 38-5 እና 6
):: የዘር ቅጠሎችን ቢጫ መሆን ተከትሎ ቀሪውም ቅጠል ወደ ቢጫነት መቀየር ትክክለኛውን
የምርት መሰብሰቢያ ደረጃን ያመለክታል (ምስል 39-1 )፡፡ ቅጠሎች በሙሉ ቢጫ ከሆኑ በኋላ
አዝመራው ሳይሰበሰብ ከቀር፤ ቅጠሎች በሙሉ ይረግፉና ፍሬዎች በንክኪም ሆነ በንፋስ
መርገፍ ይጀምራሉ (ምስል 39- 2)፡፡
የዘሩን ጭንቅላት መልክ ለውጥ ከማስተዋል በተጨማሪ፤ ሰብሉ ለመሰብሰብ መድረሱን
ለማረጋገጥ የዘር ጭንቅላቱን ጭብጥ አድርጎ መያዝና መልቀቅ፡፡በሚለቀቅበት ወቅት በመዳፍ
ውስጥ ዘር ከረገፈና ይህ የረገፈው ዘር በፊት ጥርስ ሲነከስ የመሰበር ድምጽ ካሰማ አዝመራው
ለመሰብሰብ ደርሷል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ምርቱን ሰብስቦ በነፋሻማ ቦታ ማስጣት
ያስፈልጋል፡፡ እንደ አማራጭ ደግሞ ፍሬውን በሌባ ጣትና በአውራ ጣት ጥፍር መካከል ጫን
ተደርጎ ሲያዝ የማይሰረጉድ ከሆነ ለመሰብሰብ ደርሷል ማለት ነው፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል