Page 45 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 45
36
2
.
7.2. ምርት አሰባሰብና አወቃቅ
7
.
ወ
ቅ
ሰ
ባሰ
ብ
ም
ር
ት አ
ቃ
ና አ
በተለያዩ ምክንያቶች ምርት ከመሰብሰቡ በፊት ቅጠሎች ሙሉ በሙሉ ከረገፉ፤ ምርት
ለመሰብሰብ ተስማሚው ጊዜ ጠዋት ነው፡፡ ምክንያቱም የፍሬው እራስ ሌሊቱን ውሃ ስለሚስብ
በምርት ስብሰባ ወቅት ዘሩ አይረግፍም፡፡ የኬነዋ ምርት ለመሰብሰብ በደረሰበት ወቅት
የሚኖረውን የአየር ሁኔታ በንቃት መከታተል ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ለመሰብሰብ የደረሰ
ኬነዋ ዝናብ ከነካው ዘሩ እተክሉ ጭንቅላት ላይ እያለ ሊበቅል ይችላል፡፡
በምርት ማጓጓዝ ጊዜ እንዳያስቸግርና በማስጣጣት ወቅት ብዙ ቦታ እንዳይወስድ፤ ምርቱ
ሲሰበሰብ የዘሩን ጭንቅላት ከስሩ ቢቆረጥ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን እስከ አሁን በሃገራችን ባለው
ሁኔታ፤ በምርት ስብሰባ ወቅት ሰብሉን ከስሩ በማጭድ ወይም በገጀራ መቁረጥ የተለመደ ነው
(ምስል 40) ፡፡
ምርቱ ከተሰበሰበ በኋላ በላስቲክ ኬንዳ (ምስል 41) ወይም በሚገባ የለሰለሰ ቦታ ላይ ተሰጥቶ
እንዲደርቅ ይደረጋል፡፡በሚገባ ከደረቀ በኋላ በተሰጣበት ኬንዳ ላይ በዱላ በመደብደብ ይወቃል
(ምስል 42 )፡፡ እንደ አማራጭ፤ በውቂያ ወቅት የሚከሰተውን የምርት ብክነት ለመቀነስ
ጭንቅላቱን በከረጢት ውስጥ ከቶ በዱላ መምታት ይቻላል፡፡ ምርት ስብሰባው የተከናወነው
ተክሉ ሙሉ በሙሉ ከደረቀ በኋላ ከሆነ ወዲያውኑ እንደተሰበሰበ መውቃት ይቻላል፡፡
በመጨረሻም የተወቃው እህል ከተጣራ በኋላ ከተቻለ እርጥበት በማያሳልፍ እቃ ውስጥ
መቀመጥ አለበት (ምስል 43) ፡፡ ካልተቻለ ደግሞ በተገኘው እቃ አስገብቶ እርጥበት የማያገኘው
ቦታ ማስቀመጥ፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል