Page 39 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 39
30
ታ
በሽ
በሽታ
አብዛኞቹ ኬነዋን የሚያጠቁ በሽታዎች በሻጋታ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው፡፡ በባክቴሪያና
በቫይረሶች የሚከሰቱ በሽታዎችና ኔማቶዶች የሚፈጥሩት ችግር አነስተኛ ነው፡፡ የበሽታ መከሰት
ሁኔታና በሽታው የሚያደርሰው የጉዳት መጠን እንደ ተክሉ የእድገት መጠንና የአካባቢ ሁኔታዎች
ይለያያል፡፡ በአለም ላይ በጣም የታወቀውና ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰው የኬነዋ በሽታ “ዳውኒ
ሚልዲው” (Downy mildew) የተባለው ነው፡፡ ነገር ግን አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደ
ዳምፒንግ ኦፍ፣ ግሪን ሞልድ፣ ሊፍ ስፖት፣ ብራውን ስቴም ሮት፣ አይስፖት፣ ባክቴሪያል ስፖት፣
በቫይረስ የሚከሰቱ በሽታዎችና ኔማቶዶች ያጠቁታል፡፡
3
ዲ
7
.
ው
.
7.3.1. ዳውኒ ሚልዲው
ውኒ ሚ
. ዳ
1
ል
ለ
ጫ
ኔ
ቢ ሁ
ታ
ች
ዎ
ባ
ስ
ና ተ
ማ
ካ
ሚ አ
ሽ
የበሽታው መገለጫና ተስማሚ አካባቢ ሁኔታዎች
የበ
ገ
ው መ
ታ
ተክሉ በእድገት ደረጃ ላይ እያለ ዳውኒ ሚልዲው የሚዛመተው ስፖር በሚባሉ ጥቃቅን ብናኞች
ሲሆን፤ ተክሉ ከደረቀ በኋላ ወይም ማሳ ላይ ምንም ሰብል በማይኖርበት ጊዜ ግን በፍሬው ላይ
በሚጣበቁ ወይም በተክል ቅሪት ውስጥ በሚደበቁ ኡኡስፖር በሚባሉ ክፍሎቹ አማካኝነት
ይዛመታል፡፡ በመሆኑም በአጭር እርቀት ውስጥ በስፖር አማካይነት ሲዛመት በረጅም እረቀት
ግን በኡኡስፓር አማካይነት ይዛመታል፡፡ አሁን ባለው ከፍተኛ የኬነዋ ፍላጎት የተነሳ በሃገራትና
በአህጉራት መካከል ከፍተኛ የኬነዋ ዘር ልውውጥ አለ፡፡ ይህም የዘር ልውውጥ የበሽታ
ስርጭትን ለመግታት ሲባል የተዘረጉ ስርአቶችን ሁልጊዜ ጠብቆ ስለማያልፍ በበሽታ የተበከሉ
ዘሮች ከአገር ወደ አገር የመተላለፍ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ኬነዋ በሚገኝበት ቦታ
ሁሉ ዳውኒ ሚልዲው ይገኛል ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ የዚህ በሽታ ክስተቱና(incidence)
ብርታቱ (severity) በሰብሉ ዝርያ አይነት፣ የአካባቢ ሁኔታና የሰብል እንክብካቤ አይነት
ይወሰናል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል