Page 34 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 34
25
ምስል 30 በቅጠል ላይ እየተመገበ ያለ የአፍሪካ ጓይትል
ቁጥጥር
ቁ ጥ ጥር
በማንኛውም ተባይ ቁጥጥር ውስጥ የተባይ አሰሳ የመጀመሪያው ስራ መሆን አለበት፡፡ ይህ
ከሆነ ተባዩ ቁጥሩ ሳይበዛና ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱ በፊት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ
ያስችላል፡፡ ከሌሎች ሃገሮች በተገኘ መረጃ መሰረት በኬነዋ ሰብል ውስጥ በየጊዜው አሰሳ
በማድረግ፤ አለፍ አለፍ እያሉ አስር ተክሎችን መርጦ በመመርመር በአማካይ ከአስሩ
ተክሎች ላይ ከአንድ ተባይ በላይ ከተገኘ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን
በተመረጡት አስር ተክሎች ላይ የተገኘው የተባይ አማካይ ቁጥር ከአንድ በታች ከሆነ ምንም
እርምጃ መውሰድ አያስፈልግም፡፡
የማሳ ጽዳት ማለትም ከምርት ስብሰባ በኋላ ቅሪቶችን ማስወገድ፣ መሬትን አስቀድሞና
በጥልቀት በማረስ የተባዩን ሙሽራ ለጸሃይና ለተፈጥሮ ጠላቶች ማጋለጥና ተባዩ ሊመገባቸው
የሚችሉ አረሞችን ማስወገድ የአፍሪካ ጓይ ትልን ለመቆጣጠር ወይም ለመከላከል መወሰድ
የሚገባቸው ሌሎች እርምጃዎች ናቸው፡፡ በተጨማሪም የተባዩ ቁጥር ከፍተኛ ካልሆነና በጊዜ
መለየት ከተቻለ በእጅ እየለቀሙ በመግደል ተባዩን መቆጣጠር ይቻላል፡፡
እናት የአፍሪካ ጓይ ትል እንቁላሎቿን በአበባ ደረጃ ላይ ባሉ እንደ የእርግብ አተር፣ ሽንብራ፣
በቆሎ፣ ትንባሆ፣ ማሽላ ወይም የሱፍ ተክሎች ላይ መጣል ትመርጣለች፡፡ ስለዚህ እነዚህን
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል