Page 31 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 31
22
ብዙ ሰብሎችን የሚመገበው ተባይ በኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄዱ አንዳንድ ሙከራዎችና የዘር
ብዜት ማሳዎች ላይ ተከስቶ ጉዳት አድርሷል፡፡
ባ
ዩ
ለ
ች
ተ
መገ
የ
የተባዩ መገለጫዎች
ጫዎ
የአፍሪካ ጓይ ትል ሙሉ የእድገት ደረጃን ማለትም እንቁላል፣ትል፣ዕጭና ሙሽራ የሚከተል
ሲሆን፤እናት የአፍረካ ጓይ ትል የምትንቀሳቀሰው በማታ ጊዜ ሲሆን በተክል ላይ ምንም አይነት
ጉዳት አታስከትልም፡፡ ሰውነቷ ፈርጣማ ሲሆን ከክንፎቿ ጫፍ እስከ ጫፍ ያለው እርዝመት 3.8
ሳ.ሜ ይደርሳል፡፡ የፊተኛው ክንፎቿ ከኋለኞቹ በመጠኑ ያነሱ ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ክንፎቿ
ነጣያለ ቡናማ ቀለም ሲኖራቸው ዙሪያቸውን በጥቁር መስመር የተከበቡና የፊተኞቹ ክንፎች
መሃል ላይ ጥቁር ነጥብ አለባቸው (ምስል22)፡፡ እናት የአፍሪካ ጓይ ትል ብዛት ያላቸው ነጭ
እንቁላሎችን በለጋ ቅጠሎች ወይም እምቡጦች ላይ ትጥላለች፡፡ እንቁላሎቹ እንደ አየሩ ሙቀት
ሁኔታ ከ3 እስከ 5 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚፈለፈሉ ሲሆን፤የመፈልፈያ ቀናቸው ሲቃረብ
ይጠቁራሉ፡፡ የአፍሪካ ጓይ ትል ጸጉር አልባ ነው፡፡ገና የተፈለፈለ ትል ሰውነቱ ክሬም ወይም ነጭ
ቀለም ሲኖረው የጭንቅላቱ ቀለም ግን ጥቁር ነው፡፡ትሉ ለመጀመሪያዎቹ አራት ቀናት ቁመቱ
በየቀኑ በእጥፍ ይጨምራል፡፡የመጨራሻ እድገት ደረጃቸው ላይ የደረሱ ትሎች ቀለማቸው
በጣም የተለያየና (ቢጫ፣ቡናማ፣አረንጓዴ ወይም ቀይ) (ምስል23) በጎን በኩል ከጫፍ እስከ
ጫፍ የሚዘልቅ ነጣ ያለ መስመር ያለባቸው ናቸው፡፡የነዚህ ትሎች ጭንቅላት ጠቆር ያለ
ቢጫ ወይም ብርቱካናማ ቀለም አለው፡፡ ትሉ እድገቱን ጨርሶ አፈር ውስጥ በመግባት ወደ
ሙሽራነት ከመለወጡ በፊት ከ16 እስከ 17 ለሚሆኑ ቀናት ይመገባል፡፡ ከእንቁላል እስከ እናት
ያለውን የእድገት ደረጃ ለማጠናቀቅ በሞቃታማ ወቅት ከ27 እስከ 35 ቀናት የሚፈጅበት ሲሆን
በቀዝቃዛ ወቅት ይህ ቁጥር ሊጨምር ይችላል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል