Page 27 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 27
18
ምስል 15 ከበቀሉ 3 ቀናት የሆናቸው የኬነዋ ችግኞች በትከክለኛው የዘር መጠን(ሀ) ከሚገባውየዘር መጠን
በላይ (ለ)
ዝቅተኛ ከፍታ ባላቸውና የአየሩና የአፈሩ ሙቀት ከፍተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ችግኞች
በፍጥነት ስለሚያድጉ ችግኝ የማሳሳቱ ስራ ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ቀደም ብሎ ሊተገበር
ይገባል። ችግኞች በጣም ተጠጋግተው ከሆነ የበቀሉት፤ ከብቅለት በኋላ ባሉት ቀናት የውሃ እጦት
ወይም እጥረት በሚከሰትበት ወቅት ትንንሽ የዘር እራስ በመስራትእድገታቸውን ያቋርጣሉ።
በዚህን ወቅት ተክሎቹ ሊኖራቸው የሚችለው ቁመት ከ 30 ሳ.ሜ አይበልጥም (ምስል 17)።
ሰብሉ ከዚያ በኋላ ማዳበሪያም ሆነ በቂ እርጥበት ቢያገኝ እንኳን ምንም የምርትም ሆነ የእድገት
ለውጥ አያሳይም። ነገር ግን ችግኞች በተገቢው መጠን ከሳሱና የአረም ቁጥጥር ከተደረገ አፈር
ውስጥ ያለውን እርጥበት ብቻ በመጠቀም ቁመታቸውም ሆነ ምርታቸው በሚፈለገው መጠን
ይጨምራል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የእርጥበቱ መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም እንኳን የኬነዋ ተክል
ከፍተኛ ምርት ሊሰጥ የሚችል ትልቅ የዘር እራስ ይሰራል (ምስል 18) ።
ምስል 16. ችግኝ ለማሳሳት የመጀመሪያእውነተኛ የቅጠል ደረጃተስማሚነው
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

