Page 26 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 26

17




















          ምስል14. በእርሻ ወቅት የሚፈጠሩ መስመሮች ላይ አንድ አንድ እየተዘለለ ቢዘራ በመስመሮች መሃል የሚፈለገውን እርቀት
                                      ማግኘት ይቻላል

        5. 4 .    ማ ሳሳ ት
        5.4.
               ማሳሳት
        ኬነዋ ዘሩ ከተዘራ በኋላ፣ አፈሩ በቂ እርጥበት ካለው ፣ በ 24 ሠዓታት ውስጥ የሚበቅል ሲሆን፤
        ከ ሶስት እስከ አምስት ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ ከአፈር ውስጥ ብቅ ይላል (ምስል 15) ።

        በመጀመሪያዎቹ ሁለትና ሶስት ሳምንታት የኬነዋ እድገት በጣም አዝጋሚ ስለሆነ በአረም ወይም

        በእርስ በርስ ፉክክር በከፍተኛ ደረጃ ሊጠቃ ይችላል።




        ችግኝ የማሳሻ ወቅት የተክልን ቁመት፣ የምርት መድረሻ ጊዜን፣ የእህል ምርትንና ጠቅላላ ምርትን

        የሚወስን ዋና ምክንያት ነው። ኬነዋ በተፈጥሮው ከብቅለት በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ ሶስት

        ሳምንታት እድገቱ ዘግምተኛ ስለሆነ እርስ በእርሱም ሆነ በአረም ምክንያት የሚፈጠር ሽሚያን

        መቋቋም አይችልም። በመሆኑም ከብቅለት በኋላ ከስምንተኛው እስከ አስረኛው ቀናት ውስጥ
        ወይም  ሁለት  እውነተኛ  ቅጠል  ሲያወጡ  ችግኞች  በሚፈለገው  መጠን  መሳሳት  አለባቸው

        (ምስል 16) ።











 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል  የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   21   22   23   24   25   26   27   28   29   30   31