Page 23 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 23

14


        ነገር  ግን  ከሌሎች  ሃገራት  የተገኙ  መረጃዎች  እንደሚያሳዩት፤  ተክሎች  በተወሰነ  ደረጃ
        ተጠጋግተው  እንዲበቅሉ  በማድረግ፤  ምርት  ፈጥኖ  እንዲደርስ፣  ከፍተኛ  ምርት  እንዲገኝና

        ተክሎች  ቅርንጫፋማ  እንዳይሆኑ  ያደርጋል።  በመሆኑም  የተክሎችን  ቁጥር  በመጨመር

        ከሚገኘው የምርት ጭማሪ/ ፍጠነት እና የተክሎችን ቁጥር በመቀነስና ቅርንጫፋማ እንዲሆኑ

        በማድረግ ከሚገኘው የምርት ጭማሪ የትኛው ተመራጭ እንደሆነ ጥናት ሊደረግበት ይገባል።




        በመስመር በሚዘራበት ወቅት ለአንድ ሄክታር እስከ 10 ኪ.ግ በሚገባ የተጣራ ዘር ያስፈልጋል።

        ነገር ግን በዘር ወቅት አፈሩ በቂ እርጥበት ከሌለውና የግድ በደረቁ መዘራት ካለበት የሚያስፈልገው

        የዘር መጠን በእጥፍ ይጨምራል። ለዚህም ምክንያቱ በደረቅ አፈር ላይ ሲዘራ የተወሰነ የኬነዋ

        ዘር ሊሞት ስለሚችል ያንን ለማካካስ ነው። እንደ አፈሩ አይነትና የውሃ ይዘት ዘሩ አፈር ውስጥ
        ከ 3 ሳ.ሜ. በላይ መጥለቅ የለበትም። የኬነዋ ዘር ትንንሽ ስለሆነ ከላይ ከተመለከተው ጥልቀት

        በታች  ወይም  በላይ  የሚቀመጥ  ከሆነ  በድርቀት  ወይም  በውሃ  ብዛት  ሊሞት  ይችላል።  በዘር

        አጣጣል  ወቅት  (ምስል  9)  የተስተካከለ  ስርጭት  እንዲኖርና  የዘር  ብክነት  ወይም  መብዛትን

        ለማስወገድ አንድ እጅ ዘርን ከ 5- 8 እጅ ከሚሆን አሸዋ ጋር መቀላቀል ይቻላል (ምስል 10)።

        የዘሩና የአሸዋው ምጥጥን የሚወሰነው በአማካኝ የአሸዋው መጠን ሲሆን፤ የእያንዳንዱ አሸዋ

        መጠን ከእያንዳንዱ የዘር መጠን ጋር ተቀራራቢ ከሆነ የሚያስፈልገው የአሸዋ ብዛት አነስተኛ

        ከመሆኑም በላይ የተሻለ የዘር ስርጭት ማግኘት ይቻላል። የሚፈለገውን አይነት የዘር ስርጭት
        ለማግኘት ሌላው ዘዴ ደግሞ የፕላስቲክ ጠርሙስ በመጠቀም መዝራት ነው (ምስል 11) ።
















                                        የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል     የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   18   19   20   21   22   23   24   25   26   27   28