Page 20 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 20
11
በተጨማሪም የተወሰነ የሰብል ቅሪት ማሳ ላይ
መተው ዘሩ በጎርፍ እንዳይታጠብ ይረዳል።
አረምንና በአፈር ውስጥ የሚገኙ ተባዮችን
ለመቆጣጠር ማሳውን ቀደም ብሎ ማረስና ፀኃይ
እንዲመታው ማድረግ ያስፈልጋል። አለበለዚያ
ምስል 5. በእርሻና በዘር መሃል በቂ የጊዜ እርቀት
ማሳው ከታረሰ በኋላ (ምስል 5) ወዲያውኑ በዘር ካሌለ አረም ከኬነዋው ቀድሞ ይበቅላል፡፡
መሸፈን አረሞች ቀድመው እንዲበቅሉና እንዲያድጉ ስለሚያደርግ በሰብሉ ላይ እጅግ ከፍተኛ
ጉዳት ይደርሳል። መሬቱ በጣም ጥብቅ ከሆነ በጥልቀት ማረስና የአፈር ለምነትን ሊጨምሩ
የሚችሉ ተክሎችን ዘርቶ አበባ ከማውጣታቸው በፊት በመገልበጥ አፈሩ ልል እንዲሆን ማድረግ
ይቻላል። ነገር ግን በዚህ ዘዴ በቀላሉ የሚታረስ ልል አፈር ለማግኘት ማሳውን ቀደም ብሎ
በማረስ አፈር ውስጥ የተቀበረው ተክል በሚገባ መበስበስ አለበት።በሚገባ ባልታረሰና ጓል
አፈር በበዛበት ማሳ (ምስል 6) ላይ የሚተከል የኬነዋ ዘር ውሃ ከሳበ በኋላ በቀላሉ ይደርቃል።
ይህም የሚሆንበት ምክንያት ዘሩ ከአፈር ጋር የሚኖረው ንክኪ አነስተኛ ስለሆነ ነው። የኬነዋ
ዘር መጠኑ ትንሽ በመሆኑ በደንብ የታረሰና ያልጠበቀ አፈር ከመፈለጉም በላይ ከተዘራ በኋላ
አፈሩን በስሱ ደምደም በማድረግ በዘሩና በአፈሩ መካከል በቂ ንክኪ መፍጠር ያስፈልጋል።
በመሆኑም በእርሻ ወቅት አንኳሮችን በሚገባ መሰባበርና ማድቀቅ ያስፈልጋል (ምስል 7) ።
ከባድ (ሸክላማ) አፈር ላይ የላይኛው አፈር በመጠንከር መሃላቸው ጎድጎድ ያለ ቂጣ መሰል
ክፍልፋዮችን መስራቱ የተለመደ ነው። እንዲህ ያለ ሁኔታን የምንቆጣጠርበት አንደኛው መንገድ
ዘሩከመብቀሉ በፊት ኩትኳቶ (ጭፍን ኩትኳቶ) በማድረግ ነው። ነገር ግን ይህ ዘዴሊተገበር
የሚችለው ዘሩየተዘራው በመስመር ከሆነብቻ ነው።
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል