Page 18 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 18
9
4 . በ ም ር ት ላ ይ ያ ሉ ዝ ር ያ ዎ ች
4. በምርት ላይ ያሉ ዝርያዎች
በሃገራችን በምርት ላይ ያለው የኬነዋ ዝርያ ቲቲካካ የተባለው ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ተጨማሪ
ዝርያዎችን ለማውጣት እስከ አስር የሚጠጉ ዝርያዎች በሙከራ ላይ ናቸው::
5. የ አ መ ራ ረ ት ዘ ዴ
5. የአመራረት ዘዴ
በአንጻራዊነት ኬነዋ ለአለም አዲስ ሰብል ነው፡፡ በመሆኑም ያሉት የተሻሻሉ አመራረት ዘዴዎችና
የምርምር ውጤቶች በጣም ውስን በመሆናቸው ሰብሉን በተለያዩ ስነ- ምህዳሮችና ሁኔታዎች
ውስጥ ለማምረት የሚያስችል መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል:፡፡ ያሉት ውስን መረጃዎች
እንደሚያመለክቱት በሚገባ በተዘጋጀ አፈር ላይ በተዘጋጁ እርቀታቸው ከ 30 እስከ 80 ሳ.ሜ
በሆኑ መስመሮች ላይ እስከ 10 ኪ.ግ የሚደርስ የተጣራ ዘር መዝራትና ከበቀለ በኋላ ሁለት
እውነተኛ ቅጠሎችን ሲያወጣ ማረምና ማሳሳት ተመራጭ የአመራረት ዘዴ ነው፡፡ ከ 40 እስከ
200 ኪ.ግ ዩሪያ (በአንድ ጊዜ በማድረግ ወይም በዘርና በአፈር ማስታቀፍ ወቅት ከፋፍሎ)
በማድረግ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ይቻላል፡፡ ምርት በሰው ሃይል ወይም ማሽን
በመጠቀም ሊሰበሰብ ይችላል። በተስማሚ የአየር ሁኔታ (ዝናብና የአየር ሙቀት) ውስጥ ከበቀለ
ኬነዋ በአንድ ሄክታር እስከ 50 ኩንታል የሚደርስ የእህል ምርትና ከ 50 እስከ መቶ ኩንታል
የሚደርስ ለከብት መኖ የሚሆን ተረፈ ምርት እንደሚሰጥ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
5.1.
5 . 1 . የ ማ ሳ መ ረ ጣ ና የ መ ስ ክ ዝ ግ ጅ ት
የማሳ መረጣና የመስክ ዝግጅት
ከዚህ ቀደም ኬነዋ በሃገራችን የማይታወቅ ቢሆንም በቤተሰብ ደረጃ የሚዛመዱት ሰብሎችም
ሆኑየአረም አይነቶች አሉ። ስፒናች፣ ቆስጣ፣ ሬድቢት፣ ሹገር ቢት፣ ፎደር ቢት፣ አማራንተስና
ላምበስ ኳርተርስ ከኬነዋ ጋር የሚዛመዱ ሰብሎች/አረም ሲሆኑ በዚህም ዝምድና ምክንያት
በነዚህ ተክሎች ላይ የሚታዩ ተባዮች በኬነዋ ላይም ሊከሰቱ ይችላሉ።
ዴ.ሲ ማለት ዴሲ ሲመን ማለት ሲሆን የአፈርን ወይም የዉሃን ጨዋማነት ለመለካት የሚውል መስፈርት ነው፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል