Page 17 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 17

8

        ይለያያል፡፡ ኬነዋ ከሌሎች ሰብሎች የተለየ የአፈር እርጥበት ማነስን የመቋቋም ችሎታ አለው::

        አንደኛው  የዚህ  ችሎታ  መሰረት  በተፈጥሮው  ዝቅተኛ  የዉሃ  ፍላጎት  ያለው  መሆኑ  ሲሆን
        ሁለተኛው ድግሞ የዉሃ እጥረት ከተከሰተ በኋላ ውሃ በሚያገኝበት ጊዜ ሙሉ የቅጠል ዕድገትና

        የምግብ ዝግጅት (ፎቶ ሲንተሲስ) አቅሙን መልሶ ማግኘት መቻሉ ነው፡፡ በመሆኑም ሰብሉ

        ምንም የመስኖ ዉሃ በሌለባቸውና ዝቅተኛ ዝናብ በሚያገኙ በከፊል ደረቅና ደረቅ አካባቢዎች

        መመረት እንዲችል አድርጎታል፡፡



        የኬነዋ የዉሃ ፍላጎት ከ 250 (ከቦሊቪያ አካባቢ የወጡ ዝርያዎች) እስከ 1500 ሚ.ሜ (ከአንዲስ

        ሸለቆ አካባቢ የወጡ ዝርያዎች) የሚደርስ ሲሆን ምንም እንኳን ከፍተኛ የዉሃ እጥረትን መቋቋም

        የሚችል ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ የእድገት ጊዜያት በቂ እርጥበት ይፈልጋል፡፡ በቂ የአፈር
        ውስጥ እርጥበት እስካለ ድረስ ኬነዋ ከሁለት እስከ ሶስት እውነተኛ ቅጠል እስከሚያወጣበት

        ጊዜ ድረስ ተጨማሪ ዉሃም አይፈልግም:: ኬነዋ ከመነሻው ዘገምተኛ እደገት የሚያሳይ ቢሆንም

        ከፍተኛ ድርቀትን በመቋቋም እስከ 40 ሚ.ሜ እና ከዚህም በታች በሆነ እርጥበት መኖር

        ይችላል፡፡

         .
          4
           .
        3
        3.4.     የ አ ፈ ር ዓ ይ ነ ት
               የአፈር ዓይነት
        በአለም ላይ ለሌሎች  ሰብሎች ማምረቻነት ሊውል በማይችል  አፈር  አይነት ላይ ሊመረቱ
        የሚችሉ የኬነዋ ዝርያዎች አሉ፡፡ ይህ አፈር ዝቅተኛ ዉሃ የማጠንፈፍና ለምነት ያለው፣ አሲድ
        (4.5 ፒ.ኤች.) ወይም ኮምጣጣ (9.5 ፒ.ኤች) የሆነ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን በሃገራችን እየተመረተ

        ያለው ዝርያ ግን መጠነኛ የመሬት ተዳፋትነት፣ ጥሩ ዉሃ የማጠንፈፍ አቅም፣ መካካለኛ ለምነትና

        ከፍተኛ ብስባሽ ባለው አሸዋማ አፈር ላይ ከፍተኛ ምርት ይሰጣል፡፡ ሆኖም ግን ዝርያው የትርፍ

        ዉሃ መንጣለል እስካለጋጠመው ድረስ በአሸዋማም ሆነ በከባድ አፈር ላይ ቢመረት ተመጣጣኝ
        ምርት ሊሰጥ ይችላል፡፡






                                        የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል     የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   12   13   14   15   16   17   18   19   20   21   22