Page 14 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 14
5
(ከእውነተኛ ቅጠል እስከ የቅርንጫፍ እንቡጥ ማውጣት) ፣ የአበባ እንቡጥ ማውጣት ሂደት
(ከቅርንጫፍ እንቡጥ እስከ ዋና አበባ እንቡጥ ማውጣት)፣ የማበብ ሂደት (ከእንቡጥ እስከ አበባ
መፍካት) የፍሬ ሂደት (ከአበባ እስከ ፍሬ መስጠት) እና የፍሬ መሙላት ሂደት (የዘር እራስ
ቀለም መቀየርና የስረኛ ቅጠሎች መድረቅ) ተብለው ሊለዩ ይችላሉ (ምስል 2) ፡፡
የኬነዋ ዘር ምንም አይነት የመኝታ ጊዜ (ዶርማንሲ) የሌለው ስለሆነ አስፈላጊው ሁኔታዎች
ከተሟሉ ገና በተክሉ ላይ እያለም ቢሆን እንኳ ሊበቅል ይችላል፡፡ ነገር ግን የጫካ ኬነዋ
ዝርያዎች ሳይበቅሉ በአፈር ውስጥ ከ ሁለት እስከ ሶስት አመታት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡
አሁን በሃገራችን እየተመረተ ያለው የኬነዋ ዝርያ ቲቲካካ የሚባል ሲሆን በአማካይ ቁመቱ ከ
100 እስከ 120 ሳ.ሜ ይደርሳል፡፡ ዝርያው ለምርት ለመድረስ በአማካኝ ሶስት ወራት የሚፈጅበት
ሲሆን፤ ምርቱ በሚደርስበት ወቅት ጠቅላላ የተክሉ ቀለም ወደ ቢጫ ወይም ቡርቱካናማነት
ይለወጣል፡፡
ምስል 2፡ የኬነዋ የእድገት ደረጃዎች ከዘር እስከ ምርት መድረስ
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል