Page 11 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 11
2
በምስል አንድ ላይ እንደተመለከተው እ.ኤ.አ በ 2004 እና 2014 ዓ.ም መካከል የአለም የኬነዋ
ምርት በ 2.5 እጥፍ የጨመረ ሲሆን፤ በተለይ ከ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ምን አልባትም የአለም
የምግብ ድርጅት ሰብሉን በአለም ላይ ለማስተዋወቅ ያደረገው ዘመቻ ተከትሎ እድገቱ በከፍተኛ
ደረጃ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይህ ከፍተኛ የኬነዋ ፍላጎት ከፍተኛ የኬነዋ ዋጋ መጨመርን
አስከትሏል:፡ ይህም ለአርሶ አደሮች ከፍተኛ የገቢ መጨመርን ከመፍጠሩም በላይ የአካባቢን
የጉልበት ዋጋ ከፍ በማድረግ አካባቢያዊ ግብይትን ያነቃቃል፡፡
በአለማችን ላይ ከባህር ወለል ጀምሮ እስከ 4000 ሜትር በሆኑ አካባቢዎች ሊበቅሉ የሚችሉ
የኬነዋ ዝርያዎች ወይም አይነቴዎች አሉ፡፡ ይህም ማለት እንደ ኢትዮጵያ በተለያየ ስነ-ምህዳሮች
ለተከፋፈሉ ሃገራት ለእያንዳንዱ ስነ- ምህዳር የሚስማሙ የኬነዋ ዝርያዎቸ አሉ፡፡ በመሆኑም
ትክክለኛው ዝርያ ወይም አይነቴ እስከተለየ ድረስ ኬነዋን የተለያየ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና
ባህላዊ አወቃቀር ባላቸው በማንኛውም የሃገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ማምረት ይቻላል ማለት ነው፡፡
ላ
ማ
ሉ ዓ
ማ
ን
ዋ
ና ግ
የ
የማንዋሉ ዓላማና ግብ
ብ
ዓ ላማ
ዓላማ
የምርትና ምርታማነት ማነቆዎችን በመፍታት የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፤
የኬነዋ ሰብል ለማምረትና ለመጠቀም አርሶ አደሮች አዳዲስ ቴክሎጂዎችን እና አሰራሮችን
በመጠቀም እንዲያመርቱ ምክረ ሀሳቦችን ተደራሽ ለማድረግ፤
በየደረጃው ያሉ የግብርና ልማት ባለሙያዎችን የኬነዋ አመራረትና አጠቃቀም ዘዴዎችና
ቴክኖሎጂዎች ጋር በማስተዋወቅ ለአርሶ አደሩ ያልተቋረጠ ክትትልና የሙያ ድጋፍ ማድረግ
እንዲችሉ አቅም ለመገንባት፤
ስለኬነዋ ሰብል በምርምር የተገኙ አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ለአርሶ
አደሩ እንዲደርሱ እና አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን በማስቻል ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ
ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በስፋት እንዲመረቱ ድጋፍ ለማድረግ፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል