Page 10 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 10
1
መግ ቢያ
መ ግ ቢ ያ
ኬነዋ በሚያስደንቅ ሁኔታ በተለያዩ የእርሻ ስነ ምህዳሮች ውስጥ ሊመረት ይችላል፡፡ ኬነዋ
በደርቅና ሞቃት ቦታዎች ፣ የአየር እርጥበቱ ከ 40 እስከ 88 % በሚደርስበት ቦታዎች እና
የአየሩ ሙቀት ከዜሮ በታች 8 ዲ.ሴ እስከ ከዜሮ በላይ 38 ዲ.ሴ በሚደርስባቸው ቦታዎች ሁሉ
መመረት ይችላል:: በተጨማሪም ከፍተኛ የውሃ እጥረትን የመቋቋም ችሎታ ስላለው በዓመት
ውስጥ ከ 100 እስከ 200 ሚ.ሜ ዝናብ ብቻ በሚያገኙ ቦታዎች ሁሉ መመረት ይችላል፡፡
ኬነዋ ሁሉንም ለሰውንት አስፈላጊ የሆኑ አሚኖ አሲድ የተሰኙ ንጥረ ነገሮችን ፣ ሌሎች
አስፈላጊ ሚኒራሎችና ቫይታሚኖችን አሟልቶ ከመያዙም በላይ ግሉቲን የተባለውንና በብዙ
ሰዎች ላይ የሆድ ህመም የሚያስከትለውን የፕሮቲን ስለማይዝ ለምግብነት ተመራጭ ነው፡፡
የኬነዋ አሚኖ አሲድ በዘሩ የውስጠኛው ክፍል ውስጥ ስለሆነ የሚገኘው፣ ከማብሰል በፊት
ዘሩን ለምግብነት ለማዋል በሚደረግ እንደ መፈተግ በመሳሰሉ ዝግጅቶች ወቅት አይቀንስም፡፡
በሌሎች ሰብሎች ላይ ግን መፈተግን የመሳሰሉ ዝግጅቶች የምግብነት ይዘትን በከፍተኛ ደረጃ
ይቀንሳሉ፡፡ በተጨማሪም ኬነዋ በጨው ምክንያት ሌሎች ሰብሎችን ማብቀል በማይችል አፈር
ላይ መብቀልና ምርት መስጠት ይችላል፡፡
በአንዲስ አካባቢ የሚገኙት ፔሩ፣ ቦሊቪያና ኢኳዶር የኬነዋ ዋና አምራች አገሮች ናቸው (ምስል
1)::ፔሩና ቦሊቪያ ብቻቸውን የአለምን ምርት 90 ከመቶ የሚሸፍኑ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት
ሰብሉ በአውሮፓ፣ በኤስያና በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ አገሮች ውስጥ እየተስፋፋ በመሄድ
ላይ ይገኛል፡፡ ኬነዋ አስቸጋሪ ሁኔታን መቋቋም በመቻሉ፤ የሰው ልጅን የምግብና የንጥረ ነገር
ፍላጎት ለማሟላት ባለው ስትራተጂክ ጠቀሜታ ምክንያት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ያለው
ተፈላጊነት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኬነዋ ለመጥፎ የአየር ጸባይ ሁኔታ የተጋለጡ ከሰሃራ በታች
ያሉ ድሃ የአፍሪካ ሃገሮች ያጋጠማቸውን የምግብ እጥረት ለመፍታት አይነተኛ መፍትሄ ይሆናል
ተብሎ ይገመታል፡፡
2 መጠን የሚለው የእያንዳንዸን አሸዋ ትንሽነት ወይም ትልቅነት ለማመላከት እንጂ ብዛቱን አይደለም
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል