Page 13 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 13
4
1. የ ሰ ብ ሉ ገ ጽ ታ ና የ መ ላ መ ድ አ ቅ ም
1. የሰብሉ ገጽታና የመላመድ አቅም
በምርት ተግባር ላይ የዋሉት የኬነዋ አይነቶች ከፍተኛ ዘረመላዊ ልዩነት ያሳያሉ፡፡ ይህም ልዩነት
በቀለም (በተክል፣ በአበባና በዘር) ፣ በአበባ ጭንቅላት ቅርጽ፣ በፕሮቲን ይዘት፣ በሳፖኒን ይዘት
እና በቅጠሎች ቢታ ሳያኒንና ካሊሲየም ኦክሳሌት ይዘት ይገለጻል፡፡ ይህም በመሆኑ ሰብሉ
በተለያዩ ስነ- ምህዳራዊ ሁኔታዎች ውስጥ (የአፈር አይነት፣ የእርጥበት መጠን፣ የሙቀት
መጠን፣ ከባህር ወለል በላይ ከፍታ፣ ውርጭ እና የአፈር ጨዋማነትና አሲድነት) መብቀልና
ምርት መስጠት ይችላል፡፡
ኬነዋ እንደ ዝርያው አይነት ቁመቱ ከ0.5 እስከ 2 ሜትር ሊደርስ ይችላል፡፡ ተክሉ ወፍራም
ቀጥ ያለና ቅርንጫፍ ያለው ወይም የሌለው እንጨታማ ግንድ ሲኖረው ቅጠሎቹ ደግሞ ሰፋፊና
የዳክዬ እግር ቅርጽ ያላቸው ናቸው፡፡ በወጣት ተክሎች ላይ የሚበቅሉ ቅጠሎች አብዛኛውን
ጊዜ አረንጓዴ ሲሆኑ የተክሉ እድሜ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ቀለማቸው ወደ ቢጫ፣ቀይ ወይም
ሃምራዊነት ይቀየራል፡፡
ስሩ አንድ ዋና ግንድ ይኖረውና ከዚያ ላይ የሚነሱ መጋቢ ስሮች በመፍጠር ብዛት ያላቸው
ቅርንጫፎች ይኖሩታል ፡፡ የዚህ አይነቱ ስር ተክሉ ለሚያሳየው ድርቅን የመቋቋም ባሕሪ
አንደኛው ምክንያት ነው፡፡
እንደ ዝርያዎች አይነት የኬነዋ ምርት መድረሻ ጊዜ ባብዛኛው ከ 110 እስከ 240 ቀናት ሊደርስ
ይችላል፡፡ የተለያዩ አካላት ኬነዋ የሚያሳያቸውን የእድገት ደረጃዎች በተለያየ ሁኔታ የሚገልጹት
ሲሆን በሳይንሳዊ ጥናቶች መሰረት ኬነዋ ከተዘራ ጀምሮ የሚኖረው እድገት በሰባት ሂደቶች
ይጠቃለላል እነዚህም፤ የብቅለት ሂደት (ከዘር እስከ ከአፈር መውጣት) ፣ የቅጠል እድገት
ሂደት (ሁለት እውነተኛ ቅጠል እስከሚያወጣ ድረስ) የቅርንጫፍ እንቡጥ ማውጣት ሂደት
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል