Page 15 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 15
6
2. የ ኬ ነ ዋ ዋ ና ዋ ና ጠ ቀ ሜ ታ ዎ ች
2. የኬነዋ ዋና ዋና ጠቀሜታዎች
ኬነዋ ዘርፈ ብዙጥቅሞች ያሉት የሰብል ዓይነት ሲሆን፣ በዋናነት የሚሰጣቸው ጥቅሞች
እንደሚከተለው ተገልጸዋል፡፡
1
.
.
2.1. ለ ም ግ ብነ ት
2
ለምግብነት
በተለምዶ ኬነዋ መጀመሪያ ተቆልቶ ይፈጭና በተለያየ መልኩ በዳቦነት በጥቅም ላይ ይውላል::
እንዲሁም ተቀቅሎ ሊበላ ይችላል፣ እንደ ሾርባ ይሰራል፣ እንደ ፓስታ ሊሰራ ይችላል፡፡
በሌሎች ሃገራት በተደረጉ ጥናቶች መሰረት 2 እጅ የኬነዋ ዱቄትን ከ 3 እጅ የስንዴ ዱቄት ጋር
በመቀላቀል ተቀባይነት ያለው ዳቦ መስራት ይቻላል:: በሌላ በኩል 3 እጅ የኬነዋ ዱቄት ከ 2
እጅ ስንዴ ጋር በመቀላቀል ለስላሳ ኬኮችን መስራት የሚቻል ሲሆን 7 እጅ ኬነዋን ከ 3 እጅ
ስንዴ ጋር በመቀላቀል ደረቅ ብስኩት ለመስራት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ በፋብሪካ
ደረጃ የሚቀነባበሩ ምግቦችም ከኬነዋ ይሰራሉ፡፡ ቅጠሉና ግንዱ ደግሞ ለከብቶች ምግብነት
ይውላል፡፡ በተለይ አንደ ዶሮና አሳማ ላሉ አንድ የጨጓራ ክፍል ላላቸው እንሰሳት ኬነዋን
መቀለብ ከፍተኛ የምርት ጭማሪ ለማግኘት ያስችላል፡፡
2. 2. የአፈር ጨዋማነት መቋቋም
2.2.
የ
ር ጨ
ፈ
አ
ነ
ቋ
ም
ዋ
ማ
ት መ
ቋ
ኬነዋ የአፈር / የዉሃ ጨዋማነትን መቋቋም ከሚችሉ የተክል አይነቶች በዋነኛነት የሚጠቀስ
ነው:: አሁን በአገራችን እየተመረተ ያለው የኬነዋ ዝርያ የጨዋማነት ይዘቱ እስከ 20 ዴ.ሲ1
በሆነ አፈር ላይ ሙሉ የምርት አቅሙን መግለጥ የሚችል ሲሆን፤ የጨዋማነት መጠኑ እስከ 40
ዴ.ሲ በሆነ አፈር ላይ ደግሞ እስከ 60 ከመቶ የምርት አቅሙን መግለጥ ይችላል፡፡ ጥናቶች
እንደሚያሳዩት ከሆነ የጨዋማነት ይዘቱ 16 ዴ.ሲ የደረሰ አፈር ከኬነዋ ውጪ በጣም ጨው
ይቋቋማሉ የሚባሉ ተክሎችን የመጉዳት አቅም አለው፡፡ ከዚህ አንጻር ሲታይ ኬነዋ በጨው
በተጠቃ አፈር ላይ በቀላሉ ሊመረት ይችላል፡፡እንዲሁም ኬነዋን ጨዋማ መሬት ላይ በመዝራትና
ምርቱ ከመድረሱ በፊት በመሰብሰብ የአፈሩን ጨዋማነት ማከም ይቻላል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል