Page 19 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 19
10
ስለዚህ እነዚህን ተባዮች ለማስወገድ ኬነዋን ለማምረት የሚመረጠው መስክ በቀደሙት ሶስት
አመታት ውስጥ ከላይ ለተዘረዘሩት ሰብሎች ማምረቻነት ያልዋለ መሆን አለበት።
ምስል 3 ትርፍ ዉሃ ማንጣፈፍ የማይችል ማሳ ላይ የበቀለ ኬነዋ
ምንም እንኳን ኬነዋ ከፍተኛ የውሃ አጠቃቀም ችሎታ ቢኖረውም ትርፍ ውሃን ግን መቌቌም
አይችልም (ምስል 3) ። በመሆኑም ኬነዋን ለማምረት የሚውል መሬት ትርፍ ውሃን ሊያንጣፍፍ
የሚችል ወይም መጠነኛ ተዳፋትነት (እስከ 3%) ሊኖረው ይገባል ። ኬነዋ ዘሩ ትንንሽ በመሆኑ
ምክንያት በዘር ወቅት አፈር ውስጥ በጣም መጥለቅ የለበት። ይህም በመሆኑ ማሳው ረባዳማ
ወይም ተዳፋትነቱ ከ 3 % ያልበለጠ ካልሆነ በስተቀር ከፍተኛ ዝናብ በሚኖርበት ወቅት ዘሩ
በቀላሉ በውሃ ሊታጠብ ወይም በደለል ሊሸፈን ይችላል (ምስል 4ሀ እና ለ) ።
ምስል 4. በዝናብ የታጠበና በተለያዩ ቦታዎች ዉሃ ያቆረ የኬነዋ ማሳ (ሀ) ዘሩ በታጠበበት ወይም
በተቀበረበት ቦታ ወይም ዉሃ ተኝቶበት በነበረበት ቦታ ብቅለት አይኖርም (ለ).
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል