Page 22 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 22
13
ዘሮች ከአንድ ሰብል ላይ ቢሰበሰቡም እንኳን ግዝፈታቸው ተመሳሳይ አይሆንም። በተለይ
ሰብሉ ተራርቆ በሚበቅልበት ወቅት በጣም ቅርንጫፋማ ይሆናል፡፡ በዚህን ጊዜ ከየቅርጫፉ
የሚገኙት ዘሮች ግዝፈት ስለሚለያይ የአበቃቀላቸውም ሁኔታ ይለያያል። በመሆኑም ዘሮችን
በየመጠናቸው መከፋፈል ይህንን ችግር ለመቀነስ ይረዳል፡፡ በዘር ወቅት የአፈሩ ሁኔታ በጣም
እርጥብ ወይም ደረቅ መሆን የለበትም። የአፈሩን የውሃ ይዘት መጠን ለማወቅ አንድ እፍኝ አፈር
ዘግኖ መጨበጥና መልቀቅ፤ በሚጨበጥበት ወቅት ውሃ ወይም ቀጭን ጭቃ በጣቶች መሀከል
ከወጣ የአፈሩ የውሃ ይዘት ከፍተኛ ነው ማለት ነው። ጭብጡ በሚለቀቅበት ወቅት አፈሩ
ብትን ካለ የውሃ ይዘቱ አነስተኛ ነው ማለት ነው። ጭብጡ ሲለቀቅ አፈሩ እንደ በሶ ተያይዞ
ከቀረ ትክክለኛ የውሃ ይዘት አለው ማለት ነው (ምስል 8)። ከተለያዩ ሃገራት የተገኙ መረጃዎች
እንደሚያሳዩት እንደ አፈሩ አይነት፣ የእርጥበት ይዘትና እንደ ዝርያው አይነት በመትከያ
መስመሮች መሃከል የሚኖረው ርቀት 20 እስከ 100 ሳ.ሜ ሊሆን ይችላል። በሃገራችን በተለያዩ
የአፈር አይነቶች ላይ ከተገኘው የሁለት አመታት ልምድ በመነሳት፤ በመስመሮች መሃከል ከ 40
ሳ.ሜ እና በተክሎች መሃከል 10 ሳ.ሜ ርቀት መጠበቅ የአረም ተጽእኖ ለመቀነስና በማሳ ውስጥ
እንደልብ እየተዘዋወሩ ለመስራት ያስችላል።
ምስል 8. አፈሩ በእጅ ሲጨበጥ (ሀ) አንደበሶ ከተያያዘ (ለ) የአፈሩ እርጥበት ለተከላ ተስማሚ
ነው
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል

