Page 25 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 25
16
ምስል,12 ዘር ከተዘራ በኋላ በስሱ አፈር ሲለብስ ምስል 13, አፈር ከለበሰ በኋላ አፈሩን በመጠኑ ማጥበቅ
ምርምር ወይም ለሰርቶ ማሳያ ካልሆነ በቀር ገመድ ወጥሮ ቀጥ ያሉ የመትከያ መስመሮችን
መስራት አስፈላጊ ካለመሆኑም በላይ የሚተከለው መሬት በሰፋ መጠን ይህ አሰራር በቀላሉ
ሊተገበር አይችልም። በመሆኑም አርሶ አደሮች ኬነዋን በመስመር ለመዝራት በእርሻ ወቅት
የሚፈጠሩትን መስመሮች እንደመዝሪያ መስመር መጠቀም ይችላሉ (ምስል 14) ። በመስመሮቹ
መሃል የሚኖረው እርቀት እንደ ድግሩስፋት ይለያያል። ድግሩ ጠባብ ከሆነና በመስመሮች
መሃከል የሚኖረው እርቀት ከ 25 ሳ.ሜ ካነሰ፤ አንድ አንድ መስመር እየዘለሉ መዝራት
ይቻላል። ወይም ደግሞ በመስመሮች መሃከል የሚኖረው ርቀት በጣም ሰፊ ወይም በጣም
ጠባብ በሚሆንበት ጊዜ በእያንዳንዱ መስመር ላይ የሚገኙትን የተክሎች መጠን በመቀነስ
ወይም በመጨመር የሚፈለገውን የተክል ብዛት ማግኘት ይቻላል።በእርሻ ጊዜ በተከታታይ
መስመሮች መሃል የሚኖረው ርቀት በጣም ጠባብ ወይም በጣም ሰፊ እንዳይሆን መጠንቀቅ
ነው እንጂ የመስመሮች መጣመም አሳሳቢ አይደለም። ዘሩ የሚዘራው ቦዩ ላይ ሳይሆን ከፍ
ብሎ ወገቡ ላይ መስመር ሰርቶ መስመሩን ተከትሎ በመዝራት ነው።
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል