Page 29 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 29
20
ማዳበሪያው የሚደረገው ሁለት እኩል ቦታ በመክፈል ነው፡፡ የመጀመሪያው ግማሽ ችግኞች
ከሳሱ በኋላ የሚደረግ ሲሆን ሁለተኛው ግማሽ ደግሞ የመጀመሪያው ግማሽ ከተደረገ በኋላ
ባሉት ከ 15 እስከ 21 ቀናት ውስጥ በቂ ዝናብ በሚጥልበት ጊዜ ዝናቡን ተከትሎ ማድረግ።
የአደራረጉ ሁኔታ ደግሞ ሰብሉ ተክሎቹ ከሚገኙበት መስመር አምስት ሳንቲ ሜትር ራቅ ብሎ
በመስመር ማድረግ ነው፡፡
6 . ሰ ብ ል ጥ በ ቃ
6. ሰብል ጥበቃ
6.1.
6 . 1 . አ ረም ቁ ጥ ጥ ር
አረም ቁጥጥር
ገና የበቀሉ የኬነዋ ችግኞችን ከአረም ለመለየት ስለሚያስቸግር በመስመር መዝራት በአረም
ወቅት የሚፈጠር ችግርን ያስቀራል (ምስል 19) ። በተለይ አመድማዶ የተባለው ከኬነዋ ጋር
ዝምድና ያለው አረም ባለበት አካባቢ፤ ሁለቱም ተክሎች በችግኝ ወቅታቸው በጣም ተመሳሳይ
ስለሆኑ (ምስል 20) ከብቅለት በኋላ ባሉት ሁለትና ሶስት ሳምንታት ውስጥ የሚደረግ አረም
ቁጥጥር በጣም አስቸጋሪና ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው። ከላይ እንደተገለጸው ኬነዋ በፍጥነት
መብቀል የሚችል ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ ሶስት ሳምንታት እድገቱ በጣም አዝጋሚ ስለሆነ
በአረም በቀላሉ ይጠቃል።
ስለዚህ ምንም እንኳን ኬነዋ ብዙ እንክብካቤ የማይፈልግ ሰብል ቢሆንም፣ በመጀመሪያው
የእድገት ደረጃው ላይ በእጅ በመንቀል ወይም በኩትኳቶ ከአረም ነጻ መደረግ አለበት፡፡ አረምን
በበቂ ሁኔታ ለመቆጣጠር የመጀመሪያ እርምጃ መሆን ያለበት ከፍተኛ የአረም ችግር እንዳለበት
የሚታወቅ ማሳ ላይ ያለመዝራት ነው፡፡ በተጨማሪም የማሳ ዝግጅት አስቸጋሪ አረሞችን
ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ ማለትም ቀደም ብሎና ደጋግሞ በማረስ መከናወን አለበት::
አለበለዚያ ግን አረሞች ከተክሉ እኩል ወይም በፈጠነ ሁኔታ ስለሚያድጉ ከፍተኛ ችግር
ይፈጥራሉ (ምስል 21) ፡፡ ከበቀለ ከሶስት ሳምንት በኋላ ግን ኬነዋ በፍጥነት ማደግ ስለሚጀምር
አረምን መጨቆን ከመቻሉም በላይ ከአፈር ውስጥ በትነት የሚጠፋው ውሃ ይቀንሳል፡፡ እዚህ
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል