Page 28 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 28

19
















        ምስል. 17 በመጀመሪያዎቹ 3 ሳምንታት ከፍተኛ የምግብና ውሃ ምስል 18. በመጀመሪያዎቹ 3 ሳምንታት ውስጥ በጥሩ ሁኔታ
            አጥረት ስላጋጠመው ያለጊዜው ያፈራ የኬነዋ ተክል  የተያዘ የኬነዋ ማሳ ከዚያ በኋላ የዉሃ እጥረት ቢኖርም እንኳን
                                                     ምርቱ ብዙም አይቀንስም














                            ምስል19.ከብቅለት በኋላ ባሉት ቀናት ሰብሉን ከአረም
                             ለመለየት እንዲቻል በመስመር መዝራት ያስፈልጋል
        5. 5.    የ ማ ዳ በ ሪ ያ መ ጠ ን ና አ ጠ ቃ ቀ ም ዘ ዴ
        5.5.
               የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀም ዘዴ
        ኬነዋ  ለምነታቸው  አነስተኛ  በሆኑና  ለሌሎች  ሰብሎች  አስቸጋሪ  በሆኑ  የአፈር  አይነቶች  ላይ

        የመብቀልና ምርት የመስጠት አቅም አለው። ምንም እንኳን ኬነዋ ያለ ማዳበሪያ ተቀባይነት

        ያለው ምርት መስጠት ቢችልም፤ የተለያዩ የጥናት ጽሁፎች አንደሚያሳዩት እንደ አፈሩ ሁኔታ ከ

        40 እስከ 200 ኪ.ግ ናይትሮጅን በሄክታር ቢደረግበት ምርቱ በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል። ነገር

        ግን ኬነዋ ፎስፈረስ ማዳበሪያ ቢደረግበት ምንም የምርት ጭማሪ አያሳይም። አሁን ባለው ሁኔታ
        በአገራችን በኬነዋ ላይ የተደረገ የማዳበሪያ ጥናት ስለሌለ ለጊዜው ከ 100 ኪ.ግ ናይትሮጅን

        በሄክታር እየተደረገ ነው ያለው። ይህም የተደረገበት ምክንያት ኬነዋ በዝቅተኛ ናይትሮጅንም

        ቢሆን የምርት ጭማሪ ስለሚያሳይና የአነስተኛ አርሶ አደሮችን ማዳበሪያ የመግዛት አቅም ግምት

        ውስጥ በማስገባት ነው።



 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል  የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   23   24   25   26   27   28   29   30   31   32   33