Page 24 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 24
15
ምስል 9. በባዶ እጅ ዘር ሲዘራ
ምስል 10. ከአምስት እጅ አሸዋ ጋር የተቀላቀለ የኬነዋ ዘር
በዚህ አዘራር ዘዴ ጥሩ ውጤት ለማግኘት ለዘር ማውጫ ተብሎ በክዳኑ ላይ የሚሰራው ቀዳዳ
በጣምም እንዳይተልቅ በጣምም እንዳያንስ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ቀዳዳው የሚሰራው
በሚስማር በመብሳት ከሆነ የብሱ አቅጠጫ ከክዳኑ የውስጠኛው ክፍል ወደ ውጨኛው
ክፍል መሆን አለበት። ዘሩ ከፈሰሰ በኋላ ውፍረቱ ከሁለት ሳ.ሜ በላይ ባልሆነ አፈር መሸፈን
(ምስል 12) ፈጣንና ወጥ የሆነ የዘር ብቅለት እንዲኖር ያስችላል። ዘሩ አፈር ከተመለሰበት
በኋላ በእጅ ወይም በእግር ጫን ጫን ማድረግ (ምስል 13) በዘሩና በአፈርመካከል የሚገኘውን
አየር በማስወጣት ጥሩ ብቅለት እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ ዘሩ በዝናብ ጠብታ እንዳይታጠብ
ይረዳል።
ምስል 11. ክዳኑ በተበሳ የፕላስቲክ የውሃ መያዣ እቃ ዘር ሲዘራ
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል