Page 56 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 56
47
ፎሌት 8 25 184 25 44 388
ሪቦፍላቪን 0.114 0.08 0.318 0.061 0.27 0.165 0.146
ኒያሲን 6.269 1.9 1.52 4.496 3.363 4.957 0.479
ቫይታሚንቢ6 0.396 0.37 0.487 0.325 0.482 0.407 0.318
ቫይታሚንኢ 0.57 0.42 2.44 0.5 0.08 0.71 0.21
• በማይክሮግራም ከሚለካው ከፎሌት በስተቀር ልኬቱ በሚሊግራም ነው
ኬነዋ በሰንጠረዥ አምስት ላይ ከተመለከቱት ከሁሉም የአገዳና ብርዕ እህሎችና ጥራጥሬዎች
የበለጠ ፎስፈረስና ማግኒዚየም የሚይዝ ሲሆን የፖታሲየም ይዘቱ ደግሞ ከሁሉም የአገዳና ብርዕ
እህሎች የበለጠ ነው፡፡ በተጨማሪም ከገብስ፣ ከበቆሎ፣ ከማሽላና ከስንዴ የበለጠ ካልሲየም፣
ብረት፣ ዚንክና ኮፐር ይይዛል፡፡ ቫይታሚኖችን በተመለከተ ከሌሎች የአገዳና ብርዕ ሰብሎቸ
ጋር ሲነጻጸር ኬነዋ ከፍተኛ ሪቦፍላቪንና ፎሌት፣ ተመሳሳይ መጠን ያለው ታያሚንና አነስተኛ
ኒያሲን ይዟል፡፡ በተጨማሪም ምንም እንኳን በዝግጅትና በመብሰል ወቅት መጠኑ ቢቀንስም
ኬነዋ ከማናቸውም ሰብሎች የበለጠ ቫይታሚን ኬ ይዟል፡፡ የኬነዋ ቫይታሚን የሚገኘው በዘሩ
የውስጠኛው ክፍል ውስጥ ሲሆን ከዘሩ ላይ የሚገኘውን ሳፖኒን የተባለውን ኮምጣጣ ንጥረ
ነገር የማስወገድ ሂደት ወቅት አይቀንስም፡፡
11 . የ ም ግ ብ ዝ ግ ጅ ት ና አ ጠ ቃ ቀ ም
11. የምግብ ዝግጅትና አጠቃቀም
1 1. 1. 1 2 . 1 ሳ ፖ ኒ ን የ ማ ስ ወ ገ ድ ስ ራ
11.1. 12.1 ሳፖኒን የማስወገድ ስራ
የኬነዋ ዘር የውጨኛው ክፍል ኮምጣጣ ጣዕም ባለው ሳፖኒን በተባለ ኬሚካል የተሸፈነ ነው::
ሳፖኒን ስሙን ያገኘው ሳሙና (soap) ከሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ሲሆን ይህም የሆነበት
ምክንያት በዉሃ ውስጥ ሲበጠበጥ አረፋ ስለሚሰራ ነው፡፡ ይህ ኬሚካል ከኬነዋ በተጨማሪ
በበርካታ በሃገራችን የተለመዱ እንደ አጃ፣ አተር፤አኩሪ አተርና ሽንብራ የመሳሰሉ የሰብል
አይነቶች ውስጥም በዝቅተኛ መጠን ይገኛል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል