Page 61 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 61

52
        የኬነዋ የምግብ ዝግጅት የሚጀመረው እንደማንኛውም እህል ሁሉ ከእህሉ ጋር የተቀላቀሉትን

        ቆሻሻዎች በሰፌድ በማነፈስ ወይም በእጅ በመልቀም ነው (ምስል 47-1 እና 2)፡፡ ከዚያም ዘሩ

        ከመሸክሸኩ በፊት ሳፖኒን ያለበት የዘሩ የውጨኛው ክፍል እንዲሰነጣጠቅና በፍተጋ በቀላሉ

        እንዲወገድ  እህሉ  ጸሃይ  ላይ  እንዲሰጣ  ይደረጋል  (ምስል  47-3)፡፡  ፀሃይ  ሲመታው  የሚግል

        ማስጫ  እቃ  መጠቀምና  የጸኃይ  ግለት  ከፍተኛ  በሚሆንበት  ሰዓት  ማስጣት  ጥሩ  ውጤት

        ያስገኛል፡፡ እህሉ ጸሃይ ከመታው በኋላ እዛው እተሰጣበት ቦታ እንዳለ እየቀነሱ ፀሐይ በመታው

        ሙቀጫ  መሸክሸክ  ሳፖኒኑ  በቀላሉ  እንዲለቅ  ይረዳል  (ምስል  47-4)፡፡  ኬነዋው  በሚገባ
        ከተፈተገ በኋላ በሰፌድ በማንፈስ ከዘሩ የተላቀቀው ሳፖኒን በንፋስ እንዲለይ ማድረግ (ምስል

        47- 5 እና 6)፡፡ እህሉ በሚገባ ከተነፈሰ በኋላ በንፋስ ሊወገዱ የማይችሉ ዘሩ ላይ የተጣበቁ

        ደቃቅ  የሳፖንን  ብናኞች  ለማስወገድ  በንጹህ  ዉሃ  ማጠብ  (ምስል  48-  1):፡የሚቻል  ከሆነ፤

        በመጀመሪያ ሙቅ ዉሃ መጠቀምና በመቀጠል አረፋው እስኪጠፋ ዉሃውን እየቀየሩ በቀዝቃዛ

        ዉሃ ማጠብ፡፡ በመቀጠል የታጠበውን እህል በስሱ ጸሃይ ላይ ማስጣትና ቶሎ ቶሎ እያገላበጡ

        እንዲደርቅ ማድረግ (ምስል 48-2)፡፡ ኬነዋ እርጥበት ሲነካው በቀላሉ የሚበቅል (የሚያጎነቁል)

        በመሆኑ፤ በስሱ ማስጣትና ቶሎ ቶሎ ማገላበጡ ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ እህሉ በሚገባ ከደረቀ
        በኋላ  ቀጣዩ  ስራ  ወፍጮ  ቤት  ወስዶ  ማስፈጨት  ነው፡፡  ተፈጭቶ  የመጣውን  የኬነዋ  ዱቄት

        በወንፊት  መንፋትና  አቡኩቶ  (ምስል  48-  3  እና  4)  ከላይ  በተጠቀሰው  መሰረት  እንጀራ፣

        ቂጣ፣  ዳቦና  ገንፎ  መስራት  ይቻላል  ፡፡  በምግብ  ዝግጅት  ወቅት  ኬነዋውን  ከሌላ  እህል  ጋር

        በዱቄትነት ለመቀላቀል ከመሞከር ይልቅ፤ ከመፈጨታቸው በፊት መቀላቀሉ በሚገባ የተዋሃደ

        ዱቄት ለማግኘት ያስችላል፡፡














                                        የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል     የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   56   57   58   59   60   61   62   63   64   65   66