Page 59 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 59
50
11 . 2 . የ ም ግ ብ ዝ ግ ጅ ት
11.2. የምግብ ዝግጅት
እስከ አሁን ድረስ በሃገራችን ከኬነዋ ዱቄት የተለያዩ ምግቦችን በማዘጋጀት ለማህበረሰቡ
ለማስተዋወቅ ተሞክሯል፡፡ በዚህ መሰረት የኬነዋ ዳቦ፣ ቂጣ፣ ቅንጬ፣ ገንፎና እንጀራ አሰራርን
ለማስተዋወቅ ተሞክሯል (ምስል 46)፡፡ በተለይእንጀራ ላይ በተደረገ ጥናት መሰረት ሶስት
እጅ የኬነዋ ዱቄት ከ ሰባት እጅ የጤፍ ዱቄት ጋር በመቀላቀል የሚሰራ እንጀራ በጣዕሙና
በልስላሴው (መተጣጠፍ መቻል) ሙሉ በሙሉ ከጤፍ ከተዘጋጀ እንጀራ እኩል እንደሆነ
አሳይቷል፡፡ ነገር ግን የዚህ ጥናት ዋናው ግኝት ከላይ በተመለከተው መንገድ የተዘጋጀ የኬነዋ
እንጀራ በፕሮቲን፣ በቅባትና በጠቅላላ ኢነርጂ (ሃይል ሰጪነት) ይዞታው ከጤፍ ብቻ ከተሰራ
እንጀራ እንደሚበልጥ ማሳየቱ ነው፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል