Page 87 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 87
78
የዘር ወቅት
6.2.
6.2. የዘር ወቅት
በኢትዮያ በዋናው የመኸር የዘር ወቅት ከሰኔ 20 እስከ ሐምሌ 10 ድርስ ባሉት
ቀናት ተስማሚ መሆኑ በማላመድ ሥራ ተለይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ተለያይነት ባላቸው
አካባቢዎች እየታየ ማስተካከል ይቻላል፡፡ ካሚሊና በበልግ እና በመስኖ ሊመረት የሚችል
እምቅ አቅም ያለው ሰብል መሆኑን ግንዛቤ የተወሰደ ሲሆን ወቅቱን በተመለከተ
እንደየአካባቢው የተወሰነ ልዩነት ሊኖረው ይችላል፡፡
የዘር መጠንና አዘራር ዘዴ
6.3.
6.3. የዘር መጠንና አዘራር ዘዴ
የካሚሊና ዘር መጠን ትንንሽ በመሆኑ ለአንድ ሄ/ር ከ 6-8 ኪሎግራም በቂ ሲሆን የዘር
ጥልቀቱ ከ2-3 ሳንቲሜትር በማድረግ በስሱ አፈር በማልበስ መሸፈን ያስፈልጋል፡፡ ዘሩን
በብተና ወይም በመስመር መዝራት ይቻላል፡፡ ካሚሊና በመስመር ሲዘራ በሰብሎች
መካከል 10 ሳንቲ ሜትር እና በመስመር መካካል 30 ሳንቲሜትር ርቀት በመጠበቅ
የመስመሩን ትልም በመከተል ዘር በመዝራት ቡቃያው 2-3 ቅጠል ሲያወጣ /ምስል 2/
እንደ አስፈላጊነቱ ማሳሳት ይገባል፡፡ በተለያዩ አየር ንብረት አካባቢዎች የብቅለት ቀናቱ
ሰብሉ በሚያገኘው አየር ሙቀት መጠን ላይ የሚወሰን ነው፡፡ በአጠቃላይ የካሚሊና
ሰብል ከተዘራ 4ኛው ቀን ጀምሮ ብቅለት በማሳየት ከ7-9 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ
በሙሉ ይበቅላል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል