Page 86 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 86
77
6. የአመራረት ዘዴ
6. የአመ ራረት ዘዴ
የካሚሊና ሰብል አመራረት ከማሳ መረጣ በመነሣት የማሳ ዝግጅት፣ የአመራረት
ሥርዓት፣ አዘራር ዘዴ፣ ማዳበሪያ አጠቃቀም፣ ሰብል እንክብካቤ፣ ሰብል ጥበቃ እና
የድህረምርት አያያዝን የሚያካትት ሲሆን በዝርዝር ቀጥሎ ተመላክቷል፡፡
6.1. የማሳ መረጣ እና ዝግጅት
6.1. የማሳ መ ረጣ እና ዝግጅት
ካሚሊና ሰብል ለጎመን ዘር የሰብል ዓይነቶች ተስማሚ የሆኑ የአፈር ዓይነቶች ላይ
ሊለማ ይችላል፡፡ የመሬቱም አቀማመጥ ሰብሉ ተዳፋትነቱ (slop) እስከ 4% ያለውን
እና ውሃ የማያቁር በጣም ዳገታማ ያልሆነ ማሳ ይፈልጋል፡፡ እንደማንኛውም ሰብል በቂ
የሆነ የማሳ ዝግጅት ማለትም በግንቦት፣ በሰኔ እና በዘር ወቅት 3 ጊዜ መሬቱ ታርሶ
መለስለስ ይኖርበታል፡፡
የካሚሊና ምርት በሄ/ር ከ16- 27 ኩ/ል እንደሚደርስ ጥናቶች ቢያሳዩም ውሃ
በሚተኛባቸው ቦታዎች ምርቱ ከ27-32% ይቀንሳል፡፡ በመሆኑም ከካሚሊና የተሻለ
ምርትና ምርታማነት ለማግኘት የቦታ ተስማሚና ትክክለኛ የማሳ መረጣ ማድረግ
የሚጠበቅ ይሆናል፣ (Robert, 2011)፡፡ ተዳፋታማ (ከ4% በላይ) ስፍራ ላይ ሰብሉ
በቀላሉ በጎርፍ ስለሚወሰድ ምርታማነት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ አለው፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል