Page 90 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 90
81
. የ
ሰ
ዓ
ር
ብ
ረ
ት ሥ
ራ
ል አ
መ
7
7. የሰብል አመራረት ሥርዓት
ት
ፈ
ሰ
ል
ሰብል ፈረቃ፡-ካሚሊና ከተለያዩ የብርዕና አገዳ ሰብሎች ጋር በማፈራረቅ የተባይ እና
-
ረ
ቃ፡
ብ
በሸታ ጥቃት እንዳይኖር ከመከላከሉ ባሻገር የምርት መጠኑ እና የምግብ ንጥረ ነገር
ይዘት እንዲሻሻል ይረዳል፡፡ በመስክ ምልከታ ረገድ ከካሚሊና ቀጥለው የሚዘሩ ብርዕ
ሰብሎች (ስንዴ) ምርታማነቱና የምርት ጥራቱ እንደተሻሻለ አርሶ አደሮች ፡፡ ይህም
በዋነኝነት የካሚሊናው ምርት ሲደርስ ቅጠሉ ሙሉ ለሙሉ በመርገፍ ከአፈሩ ጋር
ስለሚዋሐድ የአፈሩን ለምነት በማሻሻሉ እንደሆነ አመላካች ነው፡፡ ለተከታዩም ሰብል
ትቶት የሚያልፈው የሰብሉ ተረፈ ምርት በማሳው ላይ በመበስበስ የማሳውን አፈር
ስትራክቸር በማሻሻል ውሃ የመያዝ አቅሙን ያሳድጋል፡
ዳግም ሰብል ልማት፡- ሰብሉ በባሕርይው እርጥበት አጠር ሁኔታዎችን ስለሚቋቋም
ዳግ ም ሰ ብ ል ል ማ ት ፡ -
ከተለያዩ ሰብሎች ጋር በማጎዳኘት ለዳግም ሰብል ልማት እምቅ አቅም እንዳለው
ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም በሀገራችን የሰብሉ መድረሻ ጊዜ በአማካኝ ከ100 እስከ
120 ቀናት መሆኑ በምርምር የተረጋገጠ ሲሆን፤ በሌላው ዓለም ይህንን የመድረሻ
ጊዜ በመጠቀም ለምሳሌ ከስንዴ ወይም ሌላ ብርእ ሰብል ጋር የዳግም ሰብል ልማት
አማራጭ ሆኖ ይሰራበታል፣ (Robert, 2010)፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል