Page 91 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 91
82
በቃ
ሰብል ጥ
8 . ሰብል ጥበቃ
8 .
8.1 አረም ቁጥጥር
8.1 አረም ቁጥጥር
ካሚሊና በብቅለት ጊዜው ማሳው ከአረም የፀዳ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የቡቃያ
ዕድገቱን ከጨረሰ በኋላ በተፈጥሮዉ ፈጥኖ ማሳውን በመሸፈን በራሱ ጊዜ አረምን
የመከላከልና የመቆጣጠር አቅም ያለው ሰብል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በመጀመሪያዎቹ
የብቅለት ሳመንታት አረምን የመቋቋም አቅሙ ደካማ ስለሆነ ከበቀለ 15 ቀን ጀምሮ
በየ10 ቀን ልዩነት ከ2-3 ጊዜ ሊታረም ይገባዋል ፡፡ ካሚሊና በተዘራበት ማሳ የአረም
ተግባር በጊዜው በትኩረት ማከናወን የሚጠበቅ ዐበይት ጉዳይ ነው፡፡ በመጀመሪያዉ
አረምና በሁለተኛዉ የአረም ወቅት አብሮ መኮትኮት የበለጠ ቅርንጫፍና ዛላዉን
በመጨመር በምርታማነት ላይ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
8.2. እጽዋት በሽታና ቁጥጥር ዘዴ
8 . 2 . እ ጽ ዋ ት በ ሽ ታ ና ቁ ጥጥ ር ዘ ዴ
ካሚሊና በአጠቃላይ በሽታ እና ነፍሳት የመቋቋም አቅም ያለው ሰብል ነው፡፡ ይሁን
እንጂ ካሚሊና በምርት ሂደት ከአየር እና አፈር እርጥበት ጋር በተያያዘ እስካሁን
በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ በማሳ ላይ እንዳለ ነጭ አመዳይ (mildew) በሽታ በታችኛው
የቅጠል ገጽታ፣ ግንድና ፍሬ አቃፊው ላይ /ምስል 11 ና 12 / በሽታው ሊከሠት ይችላል::
ስለሆነም የበሽታው ጥቃት እንዳይስፋፋ በተቻለ መጠን እርጥበትን የመቆጣጠር ሥራ
መሥራት ያስፈልጋል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል