Page 96 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 96

87
        በየአካባቢው በአርሶ አደሩ ዘንድ መሣሪያው ስለማይኖር በአርሶ አደሮች ባህላዊ ልምድ


        በመታገዝ  ፍሬውን  በጥርስ  በመስበር  በሚሰጠው  ቀጭ  የሚል  ድምጽ  እርጥበቱን

        መገመት  ይቻላል፡፡  በተጨማሪም  የእህል  እርጥበትን  ይዘት  መጠንን  በመስክ  ደረጃ


        በቀላሉ ለመገመት የጨው እና የጠርሙስ ዘዴን መጠቀም አንዱ አማራጭ ነው ፡፡ በዚህ

        ዘዴ  ለመጠቀም  በሚገባ  የደረቀ ባዶ  ጠርሙስ  እና  መጠኑ    ከ5-10 ማንኪያ  የደረቀ


        ብትን ጨው ማዘጋጀት እና የጠርሙሱን 3 እጅ በእህል በመሙላት እና የተዘጋጀውን

        ጨው ጨምሮ እና በቡሽ ከድኖ የተወሰነ ደቂቃ ማወዛወዝ ከዚያም የተጨመረው


        ጨው በጠርሙሱ ግድግዳ እና በእህሉ ላይ ተጣብቆ/ ተለጥፎ የሚታይ ከሆነ የምርቱ/

        ዘር  የእርጥበት መጠን ከ15 በመቶ በላይ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ይህ እርጥበት


        መጠኑ ከፍተኛ ስለሚሆን እህሉን የበለጠ በማድረቅ ለማከማቸት ወደ 10% ማውረድ

        ያስፈልጋል ፡፡




        በመጋዘን የተከማቸ ዘርን በየጊዜው መፈተሽ፣ ምርት ማክረም የግድ ከሆነ የተሻለ ደረጃ

        ላይ  ያለውን  መርጦ  ማቆየት  ይመረጣል፡፡  እንዲሁም  ያለ  ከረጢት  በሸራ  የተከማቸ


        ምርትን በየጊዜ በማገላበጥ ማናፈስ ይኖርብናል፡፡


















 የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል  የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   91   92   93   94   95   96   97   98   99   100   101