Page 98 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 98
89
ባለመጠቀም፤ የማጓጓዣው ዓይነት ምቹ ያለመሆን፤ በመሳሰሉት ሊከሠት የሚችል
ሲሆን አስፈላጊው ማድረግ ይገባል፡፡
የድህረ ምርት ተባይ፡- በድህረ ምርት አያያዝ ሥርዓት ውስጥ የሚገጥመው ተባይ
የ ድ ህ ረ ም ር ት ተ ባ ይ ፡ -
የባለአከርካሪ ተባይ (RODENTS) ሲሆን እነዚህ የአይጥ ዝርያዎች በምርት ላይ
የሚያደርሱት ጥፋት ከፍተኛ (15%) በመሆኑ ለመከላከል በሚያስችል የመከላከያ
ዘዴዎች ማስወገድ ይገባል፡፡
ባህላዊ የአይጥ መከላከያ ዘዴዎቹ፡- አይጦች ወደ ማከማቻ ውስጥ እንዳይገቡ በተቻለ
ባ ህ ላ ዊ የ አ ይ ጥ መ ከላ ከ ያ ዘ ዴ ዎ ቹ ፡ -
መጠን የማከማቻ አካባቢውን ማጽዳት፣ ማከማቻዎች አይጦችን እንዳያስገቡ አድርጎ
መሥራት፣ የአይጥ መከላከያ ቆርቆሮ / 25 ሳ.ሜ ዲያሜትር/ በ 4 ቱም የማከማቻ
መቆሚያ እግሮች ላይ ማድረግ፤ የአይጥ ወጥመድን መጠቀም፣ የጅብ ሽንኩርትን
ጨቅጭቆ ከሌላ ተለዋሽ ምግብ ጋር በማደባለቅ በመመላለሻ መንገዶችና ቀዳዳዎች
ውስጥ መጨመር፣ ማከማቻዎች በሚገባ መጠገን፤ በግድግዳ፣ አካባቢ ያሉ ስንጣቆዎች
በወለል እና በጣራ ያሉ ቀዳዳዎች በሚገባ መደፈን አለባቸው፡፡
አይጥን በኬሚካል መከላከል፡- አስገዳጅ ከሆነ የምንጠቀማቸው የኬሚካል ቁጥጥር
አ ይ ጥ ን በ ኬ ሚ ካ ል መ ከ ላ ከ ል ፡ -
/የጸረ ተባይ ዓይነት እና መጠን /ላኒራት /ብሮሚዳይሎን / የተባለውን ጸረ አይጥ
በስንዴ በመቀላቀል ወይም የተቀላቀለውን መጠቀም፣ ክሊራት የተባለውን ጸረ አይጥ
ፔሌት መጠቀም፣ በአይጦች ጉድጓድ እና በየሁለት ሜትሩ መመላለሻ መንገዳቸው
ላይ በእያንዳንዱ 100 ግራም የተዘጋጀውን ኬሚካል ሌሎች እንስሳት ሊያገኙት
በማይችሉበት ሁኔታ ማስቀመጥ፣ ዚንክ ፎስፋይድ ከስንዴ ገለባ ጋር ማቀላቀል እና
ከላይ በተገለጸው ሁኔታ በእያንዳንዱ 25 ግራም ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል