Page 81 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 81

72
        3.7. በረዶ የመቋቋም አቅም
        3 . 7 . በ ረ ዶ የ መ ቋ ቋ ም አ ቅ ም


        በተለያዩ የማለማድ ሥራ በተለይም ደግሞ በአማራ ሊቦ ከምከምና ዋድላ እንዲሁም

        በደቡብ  ኢትዮጵያ  ሆሣዕና  ሰብሉ  ከ2-3  ጊዜ  የበረዶ  ጥቃት  ደርሶበት  ተመጣጣኝ


        ምርት የሰጠ መሆኑን በ2004 ዓ.ም እና በ2005 ዓ.ም የምርት ዘመን ተረጋግጧል::

        አርሶ አደሮች የሰብሉን አቅም ሲገልጹ “ሲያይዋት ደቃቅ ለበረዶ ግን ኃያል” ናት


        ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በተደረጉ የጥናት ሥራዎች ሰብሉ በበረዶ የተለያየ አካሉ ቢቆራረጥም

        እንደገና በማገገም ተመጣጣኝ ምርት የሚሰጥ ሰብል መሆኑ ታውቋል፣ (Hossahe-


        na poultry farm cooprative feed back, 2005) and ORDA annual report,

        2005)፡፡




        3.8 ኢንዱስትሪያዊ ጠቀሜታ
        3 . 8 ኢ ን ዱ ስ ት ሪያ ዊ ጠ ቀ ሜ ታ

        የካሚሊና  ምርት  ከምግብነት  ባሻገር  ለቀለም፤  ለቅባት፤  ለዘይት፤  ለኮስሞቲክስ፣


        ለማጽጃ፤ ወዘተረፈ…ግብዓትነት ይውላል፡፡ በሀገራችን ማህበረሰቡ ለምጣድ ማሰሻነት

        ለመጠቀም  ተመራጭ  ነው  (Britton,  2010)፡፡  በተለይም  የዘይት  ይዘትና  ጥራቱን


        ከግምት  ውስጥ  በማስገባት  ሰብሉን  በማልማት  ለኢንደስትሪ  ግብዓትነት  አይነተኛ

        አማራጭ የጥሬ ምርት ግብዓት የቅባት ሰብል ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ተስፋ አለው፡፡



        3.9 ማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ
        3 . 9  ማ ህ በ ረ ሰ ባ ዊ ና ኢ ኮ ኖ ሚ ያ ዊ ጠ ቀ ሜ ታ


        የካሜሊና ሰብል በተለያየ መንገድ በመጠቀም የኢኮኖሚ አቅምን የሚጨምር ሲሆን



                                        የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል     የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል
   76   77   78   79   80   81   82   83   84   85   86