Page 21 - Road Safety Megazine 2010
P. 21

የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

                                                               ደህንነት  ግንዛቤን  ለማሳደግ  የሚተላለፉ  መልዕክቶችን
                                                               ተቀብሎ ተግባራዊ በማድረግ እና የባህሪ ለውጥ በማምጣት
        የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ                                       ራሱን ከአደጋው መጠበቅ ይኖርበታል፡፡
        የመንገድ  ትራፊክ  አደጋን  ለመከላከል  የሚደረገው  ጥረት
        ለአንድ ወይም ለተወሰኑ ተቋማት ብቻ የሚተው አይደለም፡                     የትራፊክ  ፖሊስ  አባላትም  በስራ  ላይ  በህግ  የተሰጣቸውን
        ፡ አደጋው ዘር ፣ ቀለም ፆታ ፣ እድሜ ፣ ሐይማኖት ፣ የተማረ                ሀላፊነት  ለመወጣት  የሚያደርጉትን  ጥረት    አጠናክረው
        ፣ ያልተማረ ሳይል ለጉዳት እየዳረገ የሚገኝ ነው፡፡ በመሆኑም                 ከቀጠሉበት አሁን ላይ እየተመዘገበ ያለውን ውጤት የበለጠ
        እግረኛ ፣ አሽከርካሪ ፣ ትራፊክ ፖሊስ ፣ የትራንስፖርት ዘርፍ                ማሳደግ  ያስችላልና    የመንገድ  ትራፊክ  አደጋን  ለመከላከል
        ሳይባል  ሁሉም  የድርሻውን  ሊወጣ  እንደሚገባ  የትራፊክ                  በሚደረገው  ጥረት  ውስጥ  ሁላችንም  የሚጠበቅብንን
        ፖሊስ አባላቱ የረጅም ጊዜ የስራ ላይ ልምዳቸውን በመንተራስ                  እንወጣ የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
        ጥሪ አቅርበዋል፡፡


        የመንገድ  ትራፊክ  አደጋን  ለመከላከል  በሚደረገው  ጥረት
        ውሰጥ    ’’እያየን  እየሰማን  ለምን  እንሙት  ?  ’’  ለምንስ
        አካላችን ይጉደል ? ለምንስ ንብረታችን ይውደም ?ለምንስ
        ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር እንጋለጥ ? ለምንስ ለስነ-
        ልቡናዊ  ቀውስ  እንዳረግ  ?በሚል  ጠንካራ  እሳቤ  መሳተፍ
        ተገቢ ይሆናል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥም የሀይማኖት ተቋማትና                            የመንገድ ትራፊክ አደጋን
        አባቶች ፣ የእድር አመራሮች፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች ፣ ታዋቂ                          ለመከላከል በሚደረገው
        ግለሰቦች  ፣  የሃገር  ሽማግሌዎች  ፣  መምህራን፣  የኪነጥበብ
        ባለሙያዎች  እና  ሌሎች  ባለድርሻ  አካላት  ግንባር  ቀደም                         ጥረት ውሰጥ እያየን እና
        ተሳታፊ መሆን አለባቸው፡፡                                               እየሰማን ለምን እንሙት?


        በአንድ በሆነ የከተማዋ ስፍራ ላይ የመንገድ ትራፊክ አደጋ                           ለምንስ አካላችን ይጉደል?
        ቢከሰት፤  አደጋው  የደረሰው  በእኔ  ላይ  ቢሆንስ  ?  የተጎዳው                         ለምንስ ንብረታችን
        የእኔ  ቤተሰብ  ቢሆንስ  ?ወይም  አደጋውን  ያደረስኩት  እኔ
        ብሆንስ  ?ወይም  የቅርብ  የቤተሰቤ  አካል  ቢሆንስ  ?በሚል                            ይውደም? ለምንስ
        የአደጋውን ክስተት ወደራስ አቅርቦ መመልከት ያስፈልጋል፡፡                           ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
        ያንጊዜ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ያስችላል የሚል እምነት
        አለን ሲሉ የትራፊክ ፖሊስ አባላቱ ተናግረዋል፡፡                                  ችግር እንጋለጥ? ለምንስ
                                                                           ለስነ-ልቡናዊ ቀውስ

        በአጠቃላይ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል በሚደረገው                           እንዳረግ? በሚል ጠንካራ
        ጥረት  ውስጥ  ማንኛውም  የመንገድ  ተጠቃሚው  እና  ህግ
        አስከባሪው ለመንገድ ትራፊክ ደህንነት መስፈን የበኩላቸውን                               እሳቤ መሳተፍ ተገቢ
        ጥረት ሊያደርጉ  ይገባል፡፡                                                          ይሆናል፡፡


        አሽከርካሪው  ዘወትር  በጉዞ  ወቅት  የማሽከርከር  ሙያ
        የሚጠይቀውን  ሙያዊ  ስነ-ምግባር  በተላበሰ  መልኩ
        የትራፊክ ደንብና መመሪያን አክብሮ ማሽከርከር ይኖርበታል፡
        ፡  ዘወትር  ለህሊናው  ተገዥ  መሆን  አለበት  ትራፊክ  ፖሊስ
        ኖረም  አልኖረም  ህግ  አክባሪ  መሆን  ተገቢ  ነው፡፡  ይሄም
        ተግባር የአደጋውን ክስተት ለመከላከል የራሱ የሆነ ከፍተኛ
        አስተዋፅኦ አለው፡፡

        እግረኞችም  የመንገድ  አጠቃቀም  ስርአታቸውን  ማዘመን
        ይኖርባቸዋል፡፡ዘወትር  በጉዞ  ወቅት  ጀርባን  ለተሸከርካሪ
        ሰጥቶ  ያለመጓዝ  ወይም  የግራ  መስመርን  ይዞ  የመጓዝ
        ባህልን መልመድ ይገባል፡፡ እንዲሁም ህብረተሰቡ የትራፊክ


           18                                                                                                                                                                                                                             PB
   16   17   18   19   20   21   22   23   24   25   26