Page 24 - Road Safety Megazine 2010
P. 24

የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ











                                                        የሞተር ሳይክል ትራንስፖርት


                                                                          በከተማችን



         (በታገል በቀለ)                                                      መቁጠር
        በከተማችን  የሞተር  ሳይክል  ትራንስፖርት  ተጠቃሚዎች                         [  ምንም አይነት ምልክት ሳይሰጡ በድንገት ጉዞ
        ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል:: የአደጋው መጠንም                          መጀመር፣ መጠምዘዝና መቆም
        እንዲሁ  ጨምሯል::  አዲስ  አበባ  የሞተር  ሳይክል  መንጃ                     [  የመንገድ ምልክትና ማመላከቻዎችን አለማክበር
        ፍቃድ የመስጠት አገልግሎት የተቋረጠ ቢሆንም  ከተማዋ                           [  በዋና መንገድ ለሚመጣ ሌላ ተሸከርካሪ ቅድሚያ
        ውስጥ የሚገኙ የሞተር ሳይክል ተሸከርካሪዎች ቁጥር እያደገ                          አለመስጠት
        እንደመጣ መረጃዎች ያሳያሉ:: ይህ አጭር ጽሁፍ በከተማችን                        [  በእግረኛ መንገድ ላይ ገብቶ ማሽከርከር
        አዲስ  አበባ  የሞተር  ሳይክል  አደጋ  መንስኤዎች፣  ለችግሮቹ                   [  የማሽከርከር ብቃትና ልምድ ማነስ
        ሊወሰዱ  የሚገባቸው  መፍትሄዎች፣  የባለድርሻ  አካላት                            ህጋዊ የሆነ መንጃ ፍቃድ ይዞ አለማሽከርከር
        ሚናና የጭንቅላት መከላከያ ቆብ /ሄልሜት/ አለም አቀፋዊ                         [
        እውነታዎች ላይ ዳሰሳ ያደርጋል::                                         እንዲሁም የትራፊክ ፖሊሶች ቁጥጥር አናሳ መሆን
                                                                        ዋና ዋና ናቸው::

        በሞተር ሳይክል ምክንያት የሚደርስ አደጋ መንስኤዎች
        ሞተር ሳይክል የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት አንጻር                    ከላይ በተዘረዘሩ የህግ ጥሰቶችና የቁጥጥር መላላት እንዲሁም
        ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት:: ለአብነት ያህል በመንግስት                   በሞተረኞች ጥንቃቄ ጉድለትና ተያያዥ ምክንያቶች በሌሎች
        መስሪያቤቶችና  በግል  ድርጅቶች  መልዕክት  በማድረስ                     ተሸከርካሪዎችና እግረኞች ላይ  አደጋ ያደርሳሉ::  ይህ አደጋ
        የማይተካ  ሚና  ይጫወታል::  በሌሎች  የህብረተሰብ                      በተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና
        ክፍሎች  ደግሞ  ከቦታ  ቦታ  ለመጓጓዣነት  ያገለግላል::                  የስነልቦና ችግር ይዳርጋቸዋል:: ወንጀል ከመፈጸም አንጻርም
                                                               እንዲሁ በአከባቢያቸው ባለ ህብረተሰብ ላይ የደህንነት ስጋት
        በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች ደግሞ ለሰዎች መዝናኛነት
        ስለሚከራዩት ዋነኛ የገቢ ምንጭ ነው:: በተጨማሪም ሞተር                    ይፈጥራሉ::
        ሳይክልን  መጠቀም  ከሚሰጠው  አገልግሎት  አንጻር  የነዳጅ
        ፍጆታው አነስተኛ መሆኑ ፣ በአካል ትንሽ ስለሆነ ብዙ የመኪና
        ማቆሚያ ስፍራ አለመውሰዱና በዋጋ ረገድም ዝቅተኛ መሆኑ
        ተመራጭ  ያደርገዋል::  በተቃዋራኒው  የተለያዩ  የወንጀል
        ድርጊቶች ሲፈጸምበትም ይስተዋላል :: በተለይም ከእግረኞች
        ላይ  የተለያዩ  ቁሳቁሶችን  በመንጠቅ  ወንጀሎችን  ፈጽሞ
        ማምለጥ በዋናነት ተጠቃሽ ነው:: በእርግጥ የዚህ ጽሁፍ ዋና
        አላማ በሞተር ሳይክል የሚደርስ አደጋ ላይ ትኩረት አድርጎ
        የመፍትሄ አቅጣጫዎችን መጠቆም ነው::


         በመጀመሪያ ደረጃ የአደጋ መንስኤዎችን እንመልከት:-
             [  የጭንቅላት መከላከያ ቆብ ሳያደርጉ ማሽከርከር
             [  ከተፈቀደ የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር
             [  ትእግስት ማጣት፣ ከልክ ያለፈ በራስ መተማመን
             [  በተሸከርካሪዎች መካከል እየተሸሎኮሎኩ ማለፍና
               ማሽከርከርን እንደ ልዩ ችሎታ መለኪያ አድርጎ



           21                                                                                                                                                                                                                             PB
   19   20   21   22   23   24   25   26   27   28   29