Page 26 - Road Safety Megazine 2010
P. 26
የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ
ህግ መተዋወቅ በሞተር ሳይክል የሚደርስን ሞት 30 በመቶ
ቀንሷል፡፡ በአውሮፓዊቷ ሀገር ጣሊያንም ሄልሜት የማድረግ
ህግ ከወጣ በኋላ እ.ኤ.አ በ1999 የነበረው 20 በመቶ
የመጠቀም ልማድ 96 በመቶ ደርሶ ነበር፡፡ በዛው መጠን
ይደርስ የነበረውን የጭንቅላት አደጋ መቀነስ ተችሏል፡፡
በከተማችን ተጨባጭ ሁኔታ የሞተር ሳይክል ቁጥር ከጊዜ ወደ
ጊዜ በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፤ ባለፉት አምስት አመታት
ውስጥ በሶስት እጥፍ አድጓል:: በሞተር ሳይክል ምክንያት
የሚሞተው የሰው ቁጥር በ2009 ዓ.ም ስድስት (6) የነበረ
ሲሆን በ2010 ዓ.ም ወደ ሀያ ሁለት(22) ጨምሯል:: በአሁኑ
ወቅት በመንገድ ላይ ከሚደርሰው የሞት አደጋ 5 በመቶውን
ይሸፍናል፤ ይህ ቁጥር ባለፈው ዓመት 1 በመቶ ነበር::
የአደጋው ብዛት እና የጉዳት መጠን እንዲጨምር ካደረጉት
ምክንያቶች ውስጥ የሞተር ሳይክል ሄልሜት አጠቃቀም
ዝቅተኛ መሆን (በአሽከርካሪዎች 31 በመቶ እና በተሳፋሪዎች
8 በመቶ) እንዲሁም ከፍተኛ ፍጥነት(50 በመቶ) ይጠቀሳሉ::
ይህም ግጭትንና ከባድ የራስ ቅል ጉዳትን ያስከትላል::
ስለሆነም በከተማችን እያደገ የመጣውን የሞተር ሳይክል
ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ቁጥርና የአደጋ መጠን ከግምት
ውስጥ በማስገባት የሚመለከታቸው አካላት በጥምረት
በመሆን ህግ የማስከበር፣ ግንዛቤ የማስጨበጥ እና
አስተማማኝ እና ወቅታዊ የመረጃ አያያዝ ስርአት የመዘርጋት
ስራዎችን መስራት ለነገ የማይባል ተግባር ነው፡፡
23 PB