Page 59 - Road Safety Megazine 2010
P. 59

የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

        የሚታየው የመንገድ መዘጋጋት የችግሩ አመላካች ናቸው፡፡


        ከጊዜ  ወደጊዜ  እየጨመረ  የመጣውን  የተሽከርካሪ  ብዛት
        ሊያስተናግድ  የሚችል  የመንገድ  መሰረተ  ልማት  ሳይዘረጋ
        መቆየቱ ችግሩን አባብሶታል፡፡ ከተማዋ ይህንን የተሽከርካሪ
        ቁጥር  ዕድገት  ለማስተናገድ  ዝግጁ  አልነበረችም፡፡  በዚህም
        ምክንያት አዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት የዘመናዊ ትራንስፖርት
        ችግሮች  የሚባሉትን  እንደ  ትራፊክ  መጨናነቅ፣  የትራፊክ
        አደጋ፣  የተሸከርካሪ  ማቆሚያ  ቦታ  እጥረት  የመሳሰሉት
        ችግሮች በማስተናገድ ላይ ትገኛለች፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት
        የአዲስ አበባ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ከሁለት ዓመታት
        በፊት በሥሩ አራት የተለያዩ ተቋማትን አቋቋመ፡፡ አዲስ አበባ
        የትራፊክ  ማኔጅመንት  ኤጀንሲ  ከእነዚህ  ተቋማት  መካከል
        የትራፊክ  ፍሰትና  ደኅንነት  ላይ  እንዲሰራ  በ2008  ዓ.ም.
        ተቋቋመ፡፡


        ኤጀንሲው  ላለፉት  ሁለት  ዓመታት  የትራፊክ  ፍሰት  ላይ
        የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች በማድረግ
        ላይ ይገኛል፡፡ መሻሻሎችም ታይተዋል፡፡ ሆኖም የኤጀንሲው
        የጥናት  ውጤት  እንደሚያሳየው  የተሽከርካሪ  ማቆሚያ/
        የፓርኪንግ/ እጥረት እና ለተሽከርካሪ ተብለው የተሰሩ ዋና
        ዋና  መንገዶች  ሥርዓት  በሌለው  የመንገድ  ዳር  ፓርኪንግ
        አገልግሎት በመዋላቸው በትራፊክ ፍሰት ላይ ከፍተኛ ጫና
        አሳድሯል፡፡


        ከዚህም በተጨማሪ  ከፓርኪንግ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮች
        ለአብነት  ያህል    ደርቦ  መቆም፣  በትይዩ  መቆም፣  ማቆም
        የሚከለክለውን ምልክት አለማክበር፣ የፓርኪንግ ቦታዎችን
        ለተለያዩ  አገልግሎቶች    (ለመኪና  እጥበት፣  ለዲኮር፣
        ለቡና  ጠጡ፣  ወዘተ…)  መዋላቸው፤  ደንብን  በማያከብሩ
        ተሽከርካሪዎች ላይ ወጥ ህጋዊ እርምጃ አለመወሰዱ፤  ትላልቅ
        ህንፃዎች  በቂ  እና  ተገቢ  የተሽከርካሪ  ማቆሚያ  የሌላቸው
        መሆኑና  ያላቸውም  ቢሆን  ለሌላ  አገልግሎት  እያዋሉት
        መሆናቸው  ችግሩን  አባብሰውታል፡፡  በዋና  ዋና  መንገዶች                               መገናኛ የሚገኘው ስማርት ፓርኪንግ ታወር
        ላይ  የተሽከርካሪ  ማቆሚያ  ቦታዎች  በሕገ  ወጥ  ንግድና                 ለዚህም ማሳያ የሚሆኑ ተግባራት በመንገድ ላይ አሽከርካሪ
        የግንባታ  እቃዎች  ማስቀመጫነት  መያዛቸው፤  የተበላሹ                    እንዲቆም  ባይፈለግም  ያሉት  አሽከርካሪዎች  ግን  ሥርዓት
        ተሽከርካሪዎችን  በፍጥነት  ማንሳት  አለመቻሉ  የመሳሰሉት                  ይዘው እንዲቆሙ በቀለም ቅብ የተሰሩ የጊዜያዊ ተሽከርካሪ
        ሌሎች የትራፊክ መጨናነቁን የሚያባበሱ ችግር ናቸው፡፡                      ማቆሚያ  ሳጥኖች  (Parking  box)  በመስራት  በመንገድ
                                                               ዳር  የሚቆሙ  ተሽከርካሪዎችን  ቁጥር  ለመቀነስ  እንዲሁም
        ኤጀንሲው  ከተቋቋመባቸው  ዓላማዎች  አንዱ  የተሽከርካሪ  በማስተር  ፕላኑ  ላይ  በተቀመጠው  መሰረት  71  የፓርኪን
        ማቆሚያ/ፓርኪንግ  ችግር  መፍታት  ነው፡፡  ምክንያቱም  ቦታዎች  ተለይተው  የማልማትና  የግሉ  ዘርፍ  እንዲሰማራ
        የፓርኪንግን  ችግር  የትራፊክ  ፍሰት  ላይ  አሉታዊ  ተጽኖ  የተለያዩ                    ቴክኖሎጂዎችን         የማስተዋወቅ         ሥራዎችን
        ያሳድራል፡፡  ስለዚህ  ኤጀንሲው  ይህን  ችግር  ከምንጩ  በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
        ለመቀነስ  ፖሊሲ  የማውጣት፣  ከባለድርሻ  ተቋማት  ጋር
        በቅንጅት መሥራት፣ መንግስት የፓርኪንግ መሰረተ ልማትን                     ለአብነት ያህል ባለፈው በጀት ዓመት በመገናኛና በወሎ ሰፈር
        እንዲያለማ የማድረግ፣ የግል ተቋማት መዋዕለ ንዋያቸውን                     የስማርት  ፓርኪንግ  ግንባታዎች  ተከናውነው  አገልግሎት
        በዘርፉ  እንዲያፈሱ  የማበረታታት  እና  ሌሎች  ተያያዥ                   በመስጠት  ላይ  የሚገኙ  ሲሆን  በቅርቡ  መርካቶ  አንዋር
        የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ነው፡፡                      መስጊድ  ፊትለፊት  ተጠናቅቆ  ለአገልግሎት  ዝግጁ  ሆኗል፡

           56                                                                                                                                                                                                                             PB
   54   55   56   57   58   59   60   61   62   63   64